abol tv logo
Bemistir showpage BB

የሰለሞን አዲስ ሰለባ ማነው? ተዓምር እነ ሃዊ ቤት ገብታለች! ሰሞኑን በ"በምስጢር"!

ዜና31 ሜይ 2026
በአቦል ቲቪ ተወዳጅነትን እያተረፈ ያለው “በምስጢር” ድራማ ከሰሞኑን በከፍተኛ ውጥረት እና በሚያስገርሙ ክስተቶች ተሞልቷል። እስካሁን እየተከናወኑ ያሉትን ዋና ዋና የታሪኩ ጉዳዮች እነሆ፦
Bemistir article

በአቦል ቲቪ ተወዳጅነትን እያተረፈ ያለው “በምስጢር” ድራማ ከሰሞኑን በከፍተኛ ውጥረት እና በሚያስገርሙ ክስተቶች ተሞልቷል። እስካሁን እየተከናወኑ ያሉትን ዋና ዋና የታሪኩ ጉዳዮች እነሆ፦

የሰለሞን አደገኛ ጨዋታ፡ አዲሱ ሰለባው ማነው?

ሰለሞን በውሸት እና በተንኮል የተሞላው ሕይወቱን እንደቀጠለ ነው። ከባለቤቱ ከሀዊ ጋር እየኖረ እያለ አዲስ ሰለባ የሆነችውን ሕይወትን ለማታለል እየጣረ ነው። ነገር ግን ሰለሞን አንድ ትልቅ ስህተት ሰርቷል፤ ሕይወት ቀድሞ ሰለባው የነበረችው የማህሌት እህት መሆኗን እና ለእህቷ ስትል ለመበቀል እየተዘጋጀች መሆኑን አያውቅም። ከሰሞኑን ግን የህይወት መሰወር እህቷ ማህሌትን አስጨንቋል።

የሀዊ አባት እና የቤት ሰራተኞቹ ትንቅንቅ

የሀዊ አባት በጤና እክላቸው ምክንያት በከፍተኛ ብስጭት እና በቁጭት ውስጥ ይገኛሉ። በህመማቸው ክብደት ላለማመን በመሞከር የሕክምና ክትትልንና የቤት ውስጥ እንክብካቤን እየተቃወሙ ይገኛሉ። ይህንንም ተከትሎ የመጡትን የቤት ውስጥ ተንከባካቢዎች በሙሉ በስድብና በንቀት እያባረሯቸው ነው።

የሂሩት እና ግሩም የቤት ውስጥ ሽኩቻ

በሌላ በኩል በህሩት እና በባለቤቷ በግሩም መካከል ያለው ውጥረት እየባሰ ነው። ሂሩት የሥራ ሕይወቷን በማስቀደሟ ግሩም ደስተኛ አይደለም። ከዚህም በላይ ሂሩት የምታስተምረው የራሷ ልጅ የሆነችው የፀሎት ትምህርት ቤት መሆኑ፣ ፀሎት በሌሎች ተማሪዎች እንዲትሳለቅባትና እንድትጎዳ እያደረገ በመሆኑ በቤተሰቡ መካከል ያለው አለመግባባት እየተባባሰ ሄዷል።



ተዓምር በአዲሱ ሥራዋ

ተዓምር የሀዊ ቤተሰብ ቤት ውስጥ የሕመምተኛ ተንከባካቢ ሆና ሥራዋን ጀምራለች። መጀመሪያ ላይ ከሀዊ አባት ጋር የመግባባትና የመቀራረብ ስሜት ታሳይ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን የሌሎች ተንከባካቢዎችን እጣ ፈንታ እየተጋራች በመሆኑ ሥራዋን መጥላት ጀምራለች።

ሰለሞን የሚጠብቀው በቀል ምን ይሆን? ተዓምርስ ከቤቱ ትለቅ ይሆን?
በሚስጥር ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በ አቦልቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ።


በ #MyDStv መተግበሪያ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6
በ DStv Stream መተግበሪያ የሚወዱትን ድራማዎች ይከታተሉ!