Logo
Gojwachin S1 Slim Billboard Desktop
channel logo

Gojwachin

466Reality13

ጎጇችንን መከታተያ አምስት ምክነያቶች

ዜና
30 ማርች 2021
የኢትዮጵያን አዲሱ የሰርግ ሪያሊቲ ቲቪ ማየት ጀምረዋል? ገና ካልጀመሩ አሁን እንዲጀምሩት አንዳንድ ምክንያቶች እኒህ ናቸው! ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ታይቶ የማይታወቅ የሰርግ ሪያሊቲ ቲቪ አጓጊ የአቦል ቲቪ አቅርቦት መቷል! ከተለያዩ አዳዲስ ሪያሊት አቅርቦቶች ጎጆዋችን አንዱ ነው - ስለዚህም ትርኢት ሰምተው የማያውቁ ከሆነ አትጨነቁ አለንላቹ!

ስለ ጎጇችን

ጎጇችን ሪያሊቲ ቲቪ የተሰራው ስለኢትዮጵያን ባሕል እና ቅርጽ የሰርግ ስርአትን ለማሳየት ነው። የተለያዩ ሙሽሮች ለሰርጋቸው እና የወደፊት አኗኗሯቸው ሲዘጋጁ እናይበታለን።

ማየት ያለብዎ ምክነያቶች እነዚ ናቸው!

ፍቅርን ለማክበር

በሎክዳውኑ ምክነያት ካሳለፍነው አስከፊ ዓመት በኋላ፣ እራሳችንን ለማሳረፍ ጎጇችን ውስጥ ያሉትን ጥንዶች ፍቅራቸውን በጋብቻ ፍጻሜ ሲያደርጉ እየተከተልን መዝናናት እንችላለን። ጥንዶቻችን እንዴት እንደተዋወቁ፣ ወደእጮኝነት እንዴት እንደሄዱ እናም ጋብቻቸውን ሲፈጽሙ ምን እንደተሰማቸው፣ እዚህ የደረሱበት የጉዞዋቸው ታሪክ ሁሉ ይስሙት።

ልዩ ባሕላዊ የሰርግ አከባበር ለማየት

ትርኢቱ የሚከተለው የተለያዩ የኢትዮጵያውያን ሙሽሮችን ይሆናል! ስለ ሌሎች ባሕሎች የሰርግ ስራዓት ለመማር ዝግጁ ይሁኑ ። እኛ የምንወደው ነገር? በኤትዎ ሆነው በነዚህ የተለያዩ የሰርግ ስርአቶች መዝናናት መቻልዎ።

ስለቤተሰብ ተሳትፎ ለመማር

ጎጇችን የኢትዮጵያ ቤተሰቦችን የተለያየ ወግ እና ባህል ለማየት ጥሩ ትርኢት ነው። የጎጆዋችን ሙሽሮች ከፍቅረኝነት ወደ ትዳር ሲገቡ ቤተሰብ ምን አይነት ተሳትፎ እንዳለው እናይበታለን፣ በተለያዩ ቤተሰቦች ውስጥ ሰርግ ዝግጅት ላይ ምን ምን እንደሚካሄድም እንማራለን። 

ምራቅ የሚያስውጥ ምግቡ

ስለሰርግ ስንሰማ መጀመሪያ የምናስበው ስለ ምግብ ነው! ምግብ ያለምንም ጥያቄ ትልቁ የሰርግ አስደሳች ዝግጅት ነው። አሁን ደሞ በነዚህ ልዩ ልዩ ባህላዊ ሰርጎች ውስጥ የሚቀርበው ምግብ ዝግጅቶች አስቡ። በትርኢቱ ውስጥ የሚያዪት ልዩ ምግቦች ለሚቀጥለው ዝግጅትዎ (በርግጥ ከቅርብ ቤተሰብ እና ጓደኞች ጋር ብቻ) አዲስ የምግብ አማራጭ ለመጨመር ሀሳብ ሊሆንዎ ይችላል።

ፋሽኑ

የሰርግ ትልቁ ዝግጅት የሚመጣው የአለባበስ መረጣ እንደሆነ የታወቀ ነው። ጎጇችን የባህላዊ ልብስ ሰርጉ ውስጥ ከእንግዶች እስከ ሙሽሮቹ አለባበስ ስለሚያካትት በጣም ወደነዋል! እነዚህን ሁሉ ልዩ አለባበሶችን ለማየት ጎጆዋችንን ይከተሉ።

ጎጇችን በአቦል ቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ላይ ዓርብ ከምሽቱ 2:30 እንዳያመልጥዎ::