Logo
Abol Millionaire S2
channel logo

Abol Village Millionaire

465RealityPG13

የአቦል ሚሊየነርን አዲስ ምዕራፍ ለመመልከት እነዚህን አምስት ነገሮች በማድረግ ይዘጋጁ! - አቦል ሚሊየነር

ዜና
26 ኤፕሪል 2023
ተወዳጁ የአቦል ሚሊየነር ውድድር ምዕራፍ 2 በአቦል ቲቪ ሚያዝያ 20፣ 2015 ይጀምራል!
Abol Millionaire S2 article

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው የአንድ ሚሊየን ብር የጠቅላላ እውቀት ውድድር፣ አቦል ሚሊየነር ምዕራፍ 1 ላይ የነበረው ኃይለኛ ውድድር ከተቀመጥንበት ንቅ ንቅ ሳንል ውድድሩን እንድንከታተል አድርጎናል። ይህ የአንድ ሚሊየን ብር ውድድር የተሳታፊዎችን ጠቅላላ እውቀት በመፈተን በየዙሩ እየከበደ የሚሄድ ውድድር ነበር።

በአቦል ሚሊየነር ምዕራፍ 1 የመጨረሻ ክፍል ላይ፣ ውድድሩን እየመሩ ያለፉት አብይ እና ቢኒያም ለአንድ ሚሊየን ብር ሽልማት ተወዳድረው ነበር። እናም የመጀመሪያው የአቦል ሚሊየነር አሸናፊ የሆነው አብይ የአንድ ሚሊየን ብር ተሸላሚ ነበር!

በአዲሱ ምዕራፍ የአቦል ሚሊየነር አዘጋጆች የተወዳዳሪዎች እና የተመልካቾችን አስተያየት በመቀበል አስደሳች ዜና ይዘው ቀርበዋል። ለአሸናፊው አንድ ሚሊየን ብር ከመሸለማቸው በተጨማሪ፣ ሁለተኛ ለሚወጣው ተወዳዳሪ አንድ መቶ ሺ ብር አዘጋጅተዋል!

ይበልጥ ለማየት ይሄን ይመልከቱ!

ውድ የአቦል ሚሊየነር ተመልካቾች በምዕራፍ 2 የሚቀርበውን ውድድር ተዘጋጅተው እንዲጠብቁት እነዚህን ከታች የተዘረዘሩት ነገሮች ያዘጋጁ!

  1. አንድም የአቦል ሚሊየነር ውድድር እንዳያመልጥዎ ዲኤስቲቪ ላይ መመዝገብዎን ያረጋግጡ!

ይሄን ድረ ገጽ በመጎብኘት የዲኤስቲቪ ምዝገባዎን ማካሄድ ይችላሉ።

  1. የጠቅላላ እውቀት ጥያቄዎችን በማጥናት በውድድሩ ላይ በቤትዎ ይሳተፉ!

የአቦል ሚሊየነር እይታዎን ይበልጥ አዝናኝ ለማድረግ ጥያቄዎችን በቤትዎ ለመመለስ ይሞክሩ። እንደዚህ እውቀትዎን በመፈተን በሚቀጥለው ምዕራፍ በተወዳዳሪነት ለመቅረብ ምዝገባ እንዲያደርጉ ያነሳሳዎት ይሆናል። ስለዚህ አጋጣሚውን ይጠቀሙበት።

  1. ውድድሩን ከቤተሰብ ወይም ጓደኞች ጋር የሚከታተሉት ከሆነ ይበልጥ ለመዝናናት በቡድን ይካፈሉ እና ጥያቄዎችን እየመለሱ እርስ በራስ ይወዳደሩ!

በሁለት ቡድን በመሆን የበለጠ ነጥብ የሚያመጣውን ቡድን ለመሸለም ይወዳደሩ! የውድድሩን ህግ እና ሽልማቱን ለራስዎ መዝናኛነት መጠቀም ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ተሸናፊው ቡድን የቤት ስራ ለአንድ ሳምንት ሰርቶ አሸናፊውን እረፍት መስጠት ይችላል። ወይም ተሸናፊው ቡድን ለአሸናፊው የሚወደውን ኬክ እንደ ሽልማት ማቅረብ ይችላል።

ይሄን ውድድር ለማከናወን ካቀዱ በማህበራዊ ሚዲያ ፖስት በማድረግ አቦል ቲቪን ታግ ማድረግ እንዳይረሱ!

  1. የወደዱትን ተወዳዳሪ ለመደገፍ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 1:30 ውድድሩ እንዳያመልጥዎ!

የሚደግፉትን ተወዳዳሪ ሞራል ለመስጠት በአቦል ቲቪ ማህበራዊ ሚዲያ ድጋፍዎን ኮሜንት በማድረግ ያሳውቁ! ውድድሩን በመከታተል ስለቀረቡት ፈተናዎች አስተያየትዎን ያሳውቁን።

እነዚህን እራት ነገሮች ካዘጋጁ ለአቦል ሚሊየነር ምዕራፍ 2 ዝግጁ ነኝ ማለት ይችላሉ። አሁን አዲሱን የአንድ ሚሊየን ብር ውድድር ዘና ብለው ለመመልከት ይዘጋጁ!

አቦል ሚሊየነር አርብ ሚያዚያ 20፣ 2015 ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል! ውድድሩ እንዳያመልጥዎ የአቦል ቲቪን ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከታተሉ።