Logo

በአደይ ምዕራፍ 3 የቀረቡ አምስት አስገራሚ ክስተቶች – አደይ

ዜና
21 ኤፕሪል 2023
በአደይ ምዕራፍ 3 ላይ እነዚህ አምስት ክስተቶች በጣም አስገርመውን ነበር።
Adey s3 finale article

አደይ ምዕራፍ 3 በድራማ፣ በቀል፣ ፍቅር እና በደል ከመሞላቱ የተነሳ ከመቀመጫችን ንቅንቅ ሳንል ድራማውን ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 እንድንከታተል አስገድዶን ነበር። በድራማውም ላይ ከማስገረም አልፎ የማይረሱ ክስተቶች ቀርበው ነበር። እነዚህም ክስተቶች ይሄን ይመስላሉ፦

  1. አቤል ታሰረ።

አደይ፣ የአቤልን ንጽህና ለማስመስከር መረጃ እየሰበሰበች ባለችበት ጊዜ፣ አቤል በዚህ መሀል አደይ የምታሳለፈውን ስቃይ እና በፖሊስ ጥርጣሬ እንደገባች አይቶ እጁን ለፖሊስ ሰጥቶ ነበር። የአቤል የእስርቤት ቆይታ በአጭሩ ቢቋረጥም ለአደይ ፍቅር ሲል የከፈለው መሰዋትነት ልባችንን ነክቶ ነበረ።

ይሄን ቪዲዮ በመመልከት አቤል ለፍቅር መስዋትነት ሲከፍል ይዩት!

  1. ሁንአንተ ዳኜን ሆኖ ወደ አደይ ህይወት ተመለሰ።

ሁንአንተ፣ አደይ እና አቤል በሰርጉ ቀን በድለውኛል ብሎ በማመኑ ከአቤል ጋር ተጣልቷል። በዚህም መሀል በተፈጠረው ግብ ግብ ሁንአንተ ህይወቱ እንደጠፋ ቤተሰቡን ያሳምናቸዋል። ቤተሰቡ እና ሚስቱ በሀዘን ላይ እያሉ፣ ሁንአንተ ለእራሱ ዳኜ የተሰኘ ስም ሰጥቶ እና ተዋናይ ሚስት ቀጥሮ ለበቀል ወደ አምዴ ቤተሰብ ይመለሳል።

ዳኜ፣ የአምዴ ቤተሰብን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲተዋወቅ በዚህ ቪዲዮ ይመልከቱ!

  1. የቾምቤ አባት ማንነት ይታወቃል።

ማክዳ ደብቃው የነበረው ልጇ ቾምቤ፣ ከአያቱ ጋር እንዲያድግ ኩርኩሪት ትታው እንደነበረ እናውቅ ነበር ነገር ግን የቾምቤን አባት ማንነት ያልተመለሰ ጥያቄ ነበር። በምዕራፍ 3 ላይ የቾምቤ አባት ጫማዬ ከእስርቤት ተለቆ ልጁን ፍለጋ እንደመጣ ይጋለጣል። ጫማዬ ለቾምቤ ያለው ፍቅር ጥልቅ እንደሆነ ግልጽ ነበር ነገር ግን ቾምቤ ያለበትን ከአባ መላ ለማወቅ ለየት ያለ መንገድ ነው የተጠቀመው።

የጫማዬን ለየት ያለ መልስ ፍለጋ በዚህ ቪዲዮ ይመልከቱ!

  1. ጫማዬ ራሄልን ያግታታል።

በመጨረሻ ቾምቤ የት እንዳለ አውቆ ልጁን ፍለጋ ወደ አምዴ ቤት ሲሄድ፣ ጫማዬ የጠበቀውን አይነት አቀባበል አያገኝም። ማንነቱን ባለማወቃቸው ቾምቤን አላሳይ ያሉት ወ/ሮ ሮማን ደግሞ ትልቅ ዋጋ ይከፍላሉ። ጫማዬ፣ ራሄልን በማገት ወ/ሮ ሮማን እርሱ እንደአባትነቱ የተሰማው ናፍቆት ሲሰማቸው ይረዱታል ብሎ ያምናል። ይህ እገታ ግን ምንም እንደተጠበቀው አይካሄድም።

ራሄል በጫማዬ ታግታ ያሳለፈችውን ጊዜ በቪዲዮ ላይ ይመልከቱት!

  1. ዳኜ አደይን ያግታታል።

በቀሉን ለማስፈጸም ያቀደው እቅድ እየተዘበራረቀ በምጣቱ እና ለአደይ ያለው ስሜትን መርሳት ባለመቻሉ፣ ዳኜ አደይ እንድታገባው ለማሳመን ያግታታል። አደይ ከዳኜ ጋር በእገታ የምታሳልፈው ጊዜ ላይ ስለእቅዱ እና ፍላጎቱ ይበልጥ ለማወቅ ትሞክራለች። በዚህም መካከል አቤል ያለችበትን አፈላልጎ ሊያድናት ሲል ከዳኜ ጋር የገባበት ጸብ፣ አደይ እራሷን ለመግደል እንድትሞክር ያደርጋታል።

ይህ እገታ ያቀረባቸው አስገራሚ የፍቅር ጥያቄዎችን ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ!

እንዚህ አንድ አንድ በአደይ ምዕራፍ 3 ላይ ከተመለከትናቸው አስገራሚ ክስተቶች ናቸው። እርስዎ ከነዚህ በላይ አስገርሞዎት የነበሩትን ክስተቶች በማህበራዊ ሚዲያ ድረ ገጾቻችን ኮሜንት በማድረግ ያሳውቁን።

ለበለጡ አስገራሚ እና ልብ አንጠልጣይ ክስተቶች፣ አደይ ምዕራፍ 4 በአቦል ዱካ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:00 በዲኤስቲቪ ቻናል 466 እንዳያመልጥዎ!