Logo
Enkutatash S1
channel logo

Enkutatash

465DramaPG13

የእንቁጣጣሽን አስደናቂ ገጸ ባህሪያት እንተዋወቃቸው!

ዜና
19 ጃንዩወሪ 2024
እንቁጣጣሽ ልዩ እና አስደናቂ ገጸ ባህሪያት ይዞ የሚቀርበው አዲሱ የአቦል ቲቪ ድራማ ነው።
enkutatash article

እንቁጣጣሽ የተሰኘው አጓጊ የአቦል ቲቪ ድራማ ጀምሯል። በድራማው የመጀመሪያ ሁለት ክፍል ላይ የተለያዩ አስደናቂ ገጸ ባህሪያት ቀርበው ነበር። እንቁጣጣሽ ድራማ የሚያጠነጥነው በእንቁ የተባልች አንዲት ወጣት ሴት ህይወት እና ቤተሰብ ዙሪያ ነው። እስካሁን የቀረቡት ገጸ ባህሪያት እነዚህ ናቸው

እንቁ

እንቁ በእንቁጣጣሽ ቀን የተወለደች 21 አመት ወጣት ነች።  አያቷ / እልፍነሽ ተንከባክበው ነው ያሳደጓት በህይወቷ ሁሉም ነገር የሚቀናት አይነት ሰው ነች። ነገር ግን በተደጋጋሚ የምታየው አስጨናቂ ህልም ይረብሻታል። ይህ ህልም ከቤተሰቧ ድብቅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ይሆን? ይህ ህልም ስለ ውድ አያቷ ምን አይነት ነገር ያጋልጥ ይሆን?

እልፍነሽ

/ እልፍነሽ የእንቁ አያት እና የሰፈሩ ገንዘብ አበዳሪ የሆኑ ሀይለኛ ሴት ናቸው። ክብር ከሁሉም በላይ አስፈላጊ ነው ብለው ያምናሉ። / እልፍነሽ ለእንቁ ያላቸው ፍቅር ከምንም በላይ ይበልጣል ነገር ገን በአካባቢያቸው ላሉት ሰዎች ሀይለኛ እና ኮስታራ ናቸው። የእንቁ አያት የደበቁት ምስጢር ምን ይሆን?

መዓዛ

መዓዛ የእልፍነሽ ጎረቤት እና የስምነሽ ልጅ ነች። የእንቁ እኩያ የሆነች ሰላም የተባለች ልጅ አለቻት። የመዓዛ ህይወት በሀዘን እና ትዝታ የተሞላ ነው። መዓዛን እንደዚህ በሀዘን ውስጥ እንድትኖር ያደረጋት ምንድን ይሆን?

ሰላም

ሰላም የእንቁ እኩያ የሆነች ወጣት ልጅ ነች። የመዓዛ እና በቀለ ልጅ ነች ቤተሰቧ የደበቃት ምስጢር እንዳለ በመጠርጠሯ ትናደዳለች። ሰላም ወደ ከተማ ሄዳ ህይወቷን ለመቀየር እና ጥሩ ኑሮ ለመኖር ታቅዳለች። ሰላም እና እንቁን የቤተሰቦቻቸውን ውስብስብ ታሪክ መፍታት ይችሉ ይሆን?

Enkutatash S1
enkutatash s1 poll 2

እርስዎ ከእነዚህ ገጸ ባህሪያት እስካሁን ማንን ነው የወደዱት?

እንቁ0%
እልፍነሽ 0%
መዓዛ0%
ሰላም100%

ጥቂቶቹ የእንቁጣጣሽ ገጸ ባህሪያት ይሄን ይመስላሉ። የእንቁን አስደናቂ ታሪክ ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!