channel logo
Gizat S1

በዚህ ወር እየተፋፋሙ ያሉ የአቦል ቲቪ የፍቅር ጓደኝነቶች❤️

ዜና08 ፌብሩወሪ 2026
የፍቅረኛሞች ቀን ሲቃረብ፣ በምንወዳቸው የአቦል ድራማዎች ውስጥ ያሉ ጥንዶች በፍቅር እና በፈተና መሃል ሆነው ልባችንን ሰርቀውታል። በዚህ ወር በአቦል ቲቪ እየተፏፏሙ ያሉ የፍቅር ግንጁነቶችን እነሆ:-
valentines bb

1. ኪያ እና ቢኒ (ግዛት)፦ ካልታሰበ ጅማሮ እስከ ጽኑ መደጋገፍ! 

የኪያ እና የቢኒ ታሪክ የጀመረው ኪያ በብቸኝነት ተስፋ ቆርጣ፣ መጠጊያ ፍለጋ ወደ ሊዲያ ቤት ባመራችበት በዚያ አስቸጋሪ ምሽት ነበር። ቢኒ በሊዲያ ቤት በነበረው ድግስ ላይ የተዋወቃት ሲሆን፣ ኪያ በፓር በወሰደችው ዕፅ ስትዝናና ቀጥሎም በድጊቷ ምክንያት በጸጸት ስትታመስ አብሮ የነበርው በደግነትም ከሊዲያ ጋር ያረጋጋት እና ከጎኗ የቆመው እሱ ነበር። ኪያ አሁን ላይ እናቷ ሐረግ በመጥፋቷ ምክንያት በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ባለችበት በዚህ ሰዓት፣ ቢኒ ከጎኗ በመሆን ጥንካሬ እየሆናት ነው።

2. አንለይ እና ትርሲት (ቃታ)፦ ፍቅር በአሳዳጅ እና በጭንቀት መሃል! 

በ"ቃታ" ድራማ ውስጥ የአንለይ እና የትርሲት ታሪክ የሁላችንንም ልብ አንጠልጥሏል። አንለይ በዝርፊያ ወቅት በጥይት ተመትቶ፣ የቡድኑን መሪ ሽጉጥ አጥፍቶ በጓደኞቹ እየታደነ ይገኛል። እጮኛው ትርሲት ግን አደጋው ሳይበግራት፣ ቁስሉን እያከመች እና ከአሳዳጆቹ እየደበቀችው ትገኛለች። ትርሲት አንለይ ያላት ፍቅር ከዘራፊዎች ጥይት ሊያድነው ይችል ሆን? የሚመኙትንስ ሰላማዊ ህይወት ያገኙ ይሆን?



3. ሎዛ እና አሌክስ (ዕፀ-ሕይወት)፦ የሀብት ልዩነት ያልበገረው ፍቅር!

ሎዛ የእናቷ ሰብሌ ሰራተኛ በሆነው በአሌክስ ፍቅር ወድቃለች። ግንኙነታቸውን በምስጢር ቢይዙም፣ ሰብለ ደርሳባቸዋለች። ሰብለ አሌክስን "ልጄን አትመጥንም" በማለት በንቀት የገፋችው ቢሆንም፣ አልፎ ተርፎም ገንዘብ ሰጥታው እንዲለያት ብታግባባውም አሌክስ ግን ፍቅሩን አልቀየረም። የሁለቱ ጽናት ቢቀጥልም፣ ሰብለ እስከ መቼ ዝም ብላ ትመለከታለች?

4. ኑሃሚን እና በረከት (ግዛት)፦ በትዕግስት የተገነባ አመኔታ! 

ኑሃሚን ከአሮን እና ከታዴዎስ ጋር በነበራት ግንኙነት ልቧ ክፉኛ ተሰብሮ ስለነበር፣ ለበረከት ዕድል ለመስጠት ፈርታ ነበር። ነገር ግን የበረከት ትዕግስት እና ወደምትሰራበት ምግብ ቤት በየቀኑ እየተመላለሰ ያሳየው ታማኝነት የኑሃሚንን ልብ ሊያሸንፍ ችሏል። ይሁን እንጂ ኑሃሚን ከአባቷ ጋር የገባችው "ለጊዜው ፍቅር አልጀምርም" የሚለው ቃል ኪዳን እንቅፋት እየሆነባት ነው። አባቷመርማሪ ተሾመ በዚህ ግንኙነት ደስተኛ አይደለም... የሚያውቀው ሌላ ምስጢር ይኖር ይሆን?



የትኞቹ የአቦል ቲቪ ጥንዶች የሚቀጥሉ ይመስላችኋል? አቦል ቲቪ ከሰኞ እስከ አርብ ምርጥ ምርጥ ድራማዎችን ያቀርባል።

በ #MyDStv መተግበሪያ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6

በ DStv Stream መተግበሪያ የሚወዱትን ድራማዎች ይከታተሉ፦ tinyurl.com/bdh2j9e