በግዛት ድራማ ውስጥ የኪያ ታሪክ በዚህ ወር ልብ ሰባሪም አጓጊም በሆኑ ክስተቶች ተሞልቶ ሰንብቷል። ኪያ ካለፈችበት የሱስ አረንቋ ወጥታ ራሷን ለማደስ በምታደርገው
ጥረት ላይ ከፍተኛ እንቅፋት ገጥሟታል።
ችላ መባል እና የብቸኝነት ስሜት
ኪያ ከሱስ ርቃ ቆይታ የነበረ ቢሆንም፣ በውስጧ ያለውን የባዶነት ስሜት ግን ልታሸንፈው አልቻለችም። በተለይ የሟች አባቷ ናፍቆት ክፉኛ ሲጫጫናት፣ የሚሰማትን ህመም የምታካፍለው ሰው ፍለጋ በቤቱ ውስጥ ብዙ ብትመላለስም ያገኘችው ግን "ትኩረት ፈላጊ" እና "ቀበጥ" የሚል ስድብን ነበር። ወንድሟ አሮን፣ ሰመረ እና እናቷ ሐረግ በወቅቱ ከነበረው ውጥረት አንጻር ለኪያ የሚሆን ጊዜ አልነበራቸውም። በተለይ ከእናቷ ከሐረግ ጋር ያደረጉት የመጨረሻው እጅግ መጥፎ ንግግር፣ ኪያ እናቷን ራስ ወዳድ በማለት እንድትረግማት እና ቤቷን ጥላ እንድትወጣ አድርጓታል።
ወደ ጨለማው አለም መመለስ
በዚህ የብስጭት ስሜት ውስጥ ሆና መጠጊያ ፍለጋ የሰመረ የቀድሞ ፍቅረኛ ሊዲያ ቤት አመራች። በሊዲያ ቤት በነበረ ፓርቲ ላይ አንድ ያልተጠበቀ ክስተት ተፈጠረ። ከሊዲያ ጓደኞች አንዱ ቢኒ የኪያ የሱስ ታሪክ ሳይረዳ፣ መጠጥና ዕፅ እንድትጠቀም ጋበዛት። በዚያ ሰዓት በመጠጥ የሰከረችው ኪያ፣ ራሷን መቆጣጠር አቅቷት ወደ አሮጌው ልማዷ ተመለሰች። በማግስቱ ጠዋት ከቢኒ አጠገብ ስትነቃ የተሰማት ጸጸት እና ድንጋጤ ራሷን እንድትስት ቢያደርጋትም፣ ያው ሊዲያና ቢኒ ግን በደግነት ሊያረጓጓት ሲሞክሩ አይተናል።
አስደንጋጭ ጥሪ እና የኪያ መመለስ
የእናቷ መጥፋት ያሳሰባት ኪያ፣ የነበረባትን የጸጸት ስሜት እና ኩርፊያ ወደ ጎን በመተው ወደ ቤተሰቧ ተመልሳለች። አሁን ላይ ኪያ ከቤተሰቧ ጎን ሆና እናቷን በጭንቀት እየጠበቀች ትገኛለች።
የኪያ መመለስ ለቤተሰቡ ብርታት ይሆን ወይንስ የሐረግ መጥፋት ሌላ መዘዝ ይዞ ይመጣል?
#ግዛት ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2:30 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6 እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed

