Logo
ADEY S5 Slim Billboard Desktop

የአደይ ምርጫ – አደይ

ዜና
05 ኤፕሪል 2022
አደይ ምን ትመርጥ ይሆን?

አደይ እና አቤል ከብዙ ውጣውረድ በኋላ ግንኙነታቸው ተስተካክሎ በደስታ አብረው ሆነዋል ይህ ደስታ ግን ቶሎ ሊቋጭ ነው። አቤል ለአደይ ቀለበት ለማድረግ እያቀደ ነው ግን አደይ ከሱ ጋር መሆኗን አቶ ታደሰ ሊቀበሉት አልቻሉም። አቤል በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እራሱን ለማዳመጥ እና ለማሻሻል ያደረገው ጥረት ከአደይ ጋር ያሳለፋቸውን ጊዜያቶች ይበልጥ እንዲደሰትባቸው አድርጎታል። በተጨማሪም ከቤተሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል እና ወ/ሮ ሮማን እንደሚመኙት ወላጅ እናቱን ለመተዋወቅ ወስኗል።

አደይ የአባቷን ህይወት ለማትረፍ ብዙ ፈተና እያሳለፈች ከሁንአንተ ጋር የነበራትን ውስብስብ ግንኙነት ማስተካከል ችላለች። ከብዙ ጊዜ በኋላ ስትመኘው የነበረው ፍቅርን ማግኘት በመቻሏ ደስታዋን ሳታጣጥም የአቶ ታደሰ ተቃውሞ ቀርቧል። አቶ ታደሰ አደይ ከሁንአንተ ጋር መሆን አለባት ብለው በማመናቸው የአደይን እውነትኛ ፍላጎት መረዳት አቅቷቸዋል። በዚህ ምክንያት አደይ ከባድ ምርጫ ቀርቦላታል፣ በድጋሜ የአባቷን ደስታ ትመርጣለች ወይስ ስሜቷን አድምጣ ደስታዋን ትመርጣለች?

ሁንአንተስ ከምዕራፍ ጋር የጀመረውን አዲስ ግንኙነት ትቶ በድጋሚ ከአደይ ጋር ለመሆን ይወስናል? ምዕራፍ የአደይን ምክር ሰምታ ከሁንአንተ ጋር አዲስ ግንኙነት ከጀመረች በኋላ ሁንአንተን ብታጣው ምን ታደርግ ይሆን?

አደይ ምዕራፍ 4 ለፍቅረኛሞቹ ብዙ ደስታም ፈተናም አቅርቧል። ፈተናቸውን እንዴት እንደሚያልፉ ለማወቅ አደይ ምዕራፍ 5 ዛሬ ከምሽቱ 2:00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 እንዳያመልጥዎ!