Logo
Adey S4 Slim Billboard Desktop

አደይ የአቤልን የጋብቻ ጥያቄ ትቀበላለች?

ዜና
20 ጁላይ 2023
አደይ ትልቅ ምርጫ ቀርቦላታል። የምትፈልገውን ህይወት ወይስ የአባቷን ደስታ ትመርጣለች?
adey s4 article

የአደይ እና አቤል ታሪክ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ለትዳር ጥያቄ በቅተዋል። ነገር ግን ፍቅራቸውን አጣጥመው ሳይጨርሱ የአቤልን የጋብቻ ጥያቄ የሚያበላሽ ሌላ እንቅፋት ተፈጥሯል።

ለጥቂት ጊዜ በሌላ ሰርግ ከማይወዷቸው ሰዎች ጋር ሊጋቡ፣ የእስር ፍርድ ቀርቦባቸው እና የሌሎች እቅድ እያደናቀፋቸው ቆይተው በመጨረሻ አደይ እና አቤል በደስታ አብረው መሆን ችለዋል። በዚህ አስደሳች የፍቅር ጊዜ ላይ፣ አቤል ለአደይ ስንጠብቀው የነበረውን የጋብቻ ጥያቄ በመጨረሻ ለማቅረብ አስቧል። ነገር ግን አደይ ይሄን የጋብቻ ጥያቄ እንዳትቀበል ሊያደርጋት የሚችል ነገር ተፈጥሯል።

አቶ ታደሰ የልጃቸው አደይ ህይወት በደስታ የተሞላ እንዲሆን እንደማንኛውም አባት ይመኛሉ:: ነገር ግን በአሁን ሰዓት ልባቸው በውለታ ምክንያት እውነቱን መጋፍጥ አልቻለም። ሁንአንተ ለዋለላቸው ውለታ ብለው፣ አደይ የምትወደውን ሰው ሳይሆን፣ ሁንአንተን እንድታገባ ይፈልጋሉ። ይህ ደግሞ አደይ ከአቤል ጋር የጀመረችውን የፍቅር ህይወት እያደናቀፈ ነው። አቶ ታደሰ፣ አደይ የምትፈልገውን ይረዱ ይሆን?

አደይ የቀረበላትን ትልቅ ምርጫ እንዴት ማለፍ ትችላለች? የአባቷን ቃል ተቀብላ ከምታፈቅረው ሰው ትለያለች ወይስ በመጨረሻ የራሷን ፍላጎት ሰምታ የሚቀርብላትን የጋብቻ ጥያቄ ትቀበላለች?

ከዚህ በፊት በአደይ፡

የመጨረሻውን የምዕራፍ 4 ክፍል ሀሙስ ከምሽቱ 2:00 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 በመከታተል የአደይን ምርጫ ይወቁ!