በሰርግና በፍቅረኛሞች ቀን የታጀበው ወር ቢጠናቀቅም፣ በአቦል ቲቪ ድራማዎች ውስጥ ያሉ የፍቅር ታሪኮች ግን እየረገቡ ሳይሆን ይበልጥ እየጋሉ መጥተዋል። ባለፈው ሳምንት የተመለከትናቸው ጥንዶች አሁን ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? የወሩን ማጠቃለያ እነሆ፦
1. ኪያ እና ቢኒ (ግዛት)፦ በመከራ ውስጥ የጸናው ፍቅር
2. አንለይ እና ትርሲት (ቃታ)፦ ሕይወትን ለማዳን የሚደረግ ፍልሚያ!
የአኒሌ እና የትርሲት ታሪክ ወደ አደገኛ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። አንለይን ለመያዝ ሲያድኑ የነበሩት ዘራፊዎች አሁን እጮኛውን ትርሲትን አግተው ይዘዋታል። አንለይ የትርሲት እገታ ክፉኛ ቢያሳስበውም፣ ተስፋ ሳይቆርጥ ከጓደኛው ጋር በመሆን እሷን ነፃ ለማውጣትና ከአሳዳጆቹ እጅ ለማምለጥ አደገኛ የሴራ እና የፍልሚያ ዝግጅት ላይ ይገኛል። ትርሲት በሰላም ትመለስ ይሆን?
3. ኑሃሚን እና በረከት፦ የአባት ቁጣ እና ያልተመለሱ ጥያቄዎች
ኑሃሚን እና በረከት በመካከላቸው ያለውን አመኔታ እያሳደጉ ቢሆንም፣ የአባቷ ተቃውሞ ግን ግንኙነታቸውን ጥላ እያጠላበት ቆይቷል። አባቷ የገቡትን ቃል ኪዳን በማስታወስ በዚህ ግንኙነት ላይ ያለውን ጥላቻ አልቀነሰም። ከሁሉም የሚገርመው ግን የሱ ተጠራጣሪነት ትክክለኛ ሆኖ መገኘቱ ነው። ተሾመ በረከት የሱ ልጅ መሆኑን ለእህቱ አይናለም ነግሯታል😳 ኑሃሚንስ ይሄን ስትሰማ ምን ይሰማት ይሆን?
4. ሎዛ እና አሌክስ (ዕፀ-ሕይወት)፦ ምስጢር የናወጠው ፍቅር
የሰብለ ሴራ እና ተንኮል ሎዛን እና አሌክስን ሊለያያቸው አልቻለም። አሌክስ ለፍቅራቸው ሲል ስራውን ለመልቀቅ አስቦ የነበረ ቢሆንም፣ በሎዛእና ሰብለ ግፊት እንዲቆይ ተደርጓል። ይሁን እንጂ አሁን የሎዛ እውነተኛ ወላጅ ማንነት ይፋ መውጣቱ በመላው ቤተሰቡ ላይ ትልቅ ቀውስ ፈጥሯል። ይህ አዲስ ክስተት አሌክስን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የከተተው ሲሆን፣ ፍቅራቸው ይህን አዲስ ማዕበል መቋቋም ይችል እንደሆነ አብረን እንተብቃለን!
የአቦል ቲቪ ምርጥ ምርጥ ድራማዎች ከሰኞ እስከ አርብ ይቀርባሉ!
በ #MyDStv መተግበሪያ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6
በ DStv Stream መተግበሪያ የሚወዱትን ድራማዎች ይከታተሉ!
