Logo
ADEY S5 Slim Billboard Desktop

አደይ ድራማን ለማየት 3 ምክንያቶች

ዜና
31 ኦክቶበር 2023
አደይ ድራማ ፍቅር፣ ቤተሰብ፣ ጥበብ እና ኮሜዲ ይዞልን የሚቀርበው ምርጥ የአቦል ዱካ ድራማ ነው።
adey 3 reasons to watch 2023

አደይ አስቂኝ፣ አጓጊ እና ልብ የሚነካ ድራማ ነው። ድራማው የአንዲት አደይ የተሰኘች ወጣት ሴትን ጉዞ ሲሆን። ድራማው ከአደይ ጋር የተሳሰረውን የሁለት ቤተሰብ ህይወት እና ጉዞን የሚቃኝ ነው። አደይ ድራማን ለመከታተል የበለጠ ምክንያት የሚፈልጉ ከሆነ ትክክለኛ ቦታ መጥተዋል። እነዚህ አደይ ድራማን ለመከታተል 3 ምክንያቶች ናቸው

የአደይ ገጸ ባህሪ

አደይ የድራማው ዋና ገጸ ባህሪ ብቻ ሳትሆን መላው ተመልካች እራሱን የሚያይባት ገጸ ባህሪ ነች። በችግር ጊዜ ላይ እጅ ሳትሰጥ እና ሳትደክም እራሷን አነሳስታ ማለፍ መቻልዋን ስናይ ያለፉትን የህይወት ፈተናዎች እንዴት ማለፍ እንደቻልን እናስታውሳለን። እናም አደይ በጎ አድርጎት ስታደርግ በደስታ የእራሳችንን ድርጊቶች ማስታወስ እንችላለን። ስለዚህ ማን የእራሱን መልክ የሚያሳይ ገጸ ባህሪ ማየት አይፈልግም?

የድራማው አጓጊነት

ገጸ ባህሪዎቻችን ችግራቸው የማያልቅ ናቸው። ስለዚህም የአደይ ድራማ ይዘት እውነተኛ የመሳሰሉ ታሪኮችን ይዞ ይቀርብልናል። በዚህ ሳምንት አቶ ግርማ ትልቅ የውሸት ክስ ቀርቦባቸዋል እናም ቤተሰቡ እንዴት ይሄንን መፍታት እንደሚችል በጉጉት እየተመለከትን ነው።

Abol Tv Adey S5 Poll Back
adey s5 poll 3

የችግር ሁሉ ፈቺ አደይ ይሄን ትፈታው ይሆን?

አዎ ትፈታዋለች100%
አይ አትፈታውም0%

የፍቅር ታሪኩ

አደይ እና አቤል ከተገናኙ ጀምሮ የማያጠራጥር ፍቅር በማህላቸው እንዳለ ግልጽ ነበር። ነገር ን የጥንዶቻችን የፍቅር ታሪክ እንደፍቅር ስሜታቸው ቀላል አይደለም። ያልተሳኩ ሁለት ሰርጎች፣ በሰው ምክንያት የተፈጠሩ አለመግባባቶች እናም በማላቸው ለመግባት የወሰኑ አፍቃሪዎችን አልፈው እዚ ደርሰዋል። ነገር ግን ጥንዶቻችን ቀለበት ከማሰራቸው በፊት እፎይ ማለት አንችልም። ምን ይላሉ? የአደይ እና አቤልን የፍቅር ታሪክ መጨረሻ ለማየት አደይ ድራማን መከታተል ጥሩ ምክንያት አይደለም?

Abol Tv Adey S5 Poll Back
adey s5 poll 4

እርስዎ የየትኛው ጥንዶች ደጋፊ ነብሩ?

አደይ እና አቤል 75%
አደይ እና ሁኔ25%

እነዚህ ምክንያቶች አደይ ድራማን እንዲከታተሉ እንዳሳመኗቸው እርግጠኛ ነን። አደይ ድራማን ምን ያህል እንደወደዱት የአቦል ዱካ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን በመከተል ያሳውቁን። አደይ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይቀርባል።