Logo
Nafikot Slim Billboard Desktop 1600x160

የፀሀይ እና ግሩም የተከለከለ ፍቅር

ዜና
07 ጁላይ 2021
የፀሀይ እና ግሩምን ፍቅር ቤተሰቡ አልተቀበለውም።

የፀሀይ እና ግሩም ግንኙነት በመታወቁ ቤተሰቡ እየተረበሸ ነው። አንዋር ስለ ፀሀይ እና ግሩም ግንኙነት አውቋል፣ ይህ በወንድማማቾቹ መካከል ፀብ ፈጥሯል። ግሩም ስለ ግንኙነታቸው እውነቱን ለገላ ለመንገር ፀሀይን ሲለምናት ቆይቷል፤ ግን እውነቱ መታወቁ የሚያመጣውን ነገር አልጠበቀውም።

ግሩም ከገላ ጋር ያለው ግንኙነት ለየት ያለ በመሆኑ ምክንያት፣ ለፀሀይ ያለውን ፍቅር ትቀበለዋለች ብሎ ነበር የሚያስበው -ግን ገላ መቀበል አቅቷታል። ፀሀይ የእናቷ ህመም እንዳይባባስ እና ጭንቀት እንዳይበዛባት ብላ እውነቱን ስትደብቅ እስካሁን ቆይታ ነበር። አሁን የሚጠብቃት ምርጫ ከእናቷ እና ግሩም መሀል ነው፣ ምን ትመርጥ ይሆን?

ቃልአብን ወደቤት ለመመለስ አንዋር ያመጣውን ሀሳብ ገላ አልተቀበለችውም፤ ግን ልጆችዋ ከቃልአብ ጋር እንድትገናኝ ብለው መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።

በዚህ ምክንያት ከእነዚህ ሁለት ነገሮች አንዱ ሊፈጠር ይችላል፣

1. ገላ ቃልአብን ከመናፈቋ እና በህመም ከመድከሟ የተነሳ የአንዋርን ሀሳብ ትቀበለዋለች። ይህ ከተፈጠረ ግሩም ይቀበለዋል ወይስ ፀሀይን እንዳለ ከቤት ይጠፋል?

2. ግሩም እንደተመኘው የሱን እና የፀሀይን ፍቅር ትቀበለዋለች። ቃልአብ ስለዚህ ምን ይሰማው ይሆን?

በአሁን ሰዓት ላይ ማንም የሚፈልገውን ማግኘት የሚችልበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለው።

ምንም ቢሆን ግን ገላ ፊት የቀረበው አስጨናቂ ውሳኔ ነው፤ ምን ትወስን ይሆን? ይሄን ለማወቅ ናፍቆትን ይከታተሉ!

ናፍቆት ማክሰኞ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፤ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይቀርባል!