abol tv logo

ቅናት - የተገፉት

ዜና
22 ዲሴምበር 2021
ላምሮት ውብዬን ገድላታለች።

ላምሮት በድጋሜ በቅናቷ ተመርታለች። የጴጥሮስ ብቸኛ ፍቅር ለመሆን ያላት ፍላጎት በተደጋጋሚ ውስብስብ ችግር ውስጥ ከቷታል። የመጀመሪያ ሚስቱ ፌኔትን በጴጥሮስ እና ላምሮት ቀለበት ማሰሪያ ዝግጅት ቀን እራሷን መቆጣጠር ባለመቻሏ የፌኔትን ህይወት አጥፍታለች። ይሄንን ጥፋት ለመሸፋን የፌኔት ነርስ ሩሃማን ወቅሳ አሳስራታለች።

ይሄን ይመስል ነበር፡

ይህ የሩሃማ ቤተሰብ ህይወትን አዘበራርቋል እናም የሩሃማ ልጅ ሊንዳ እናቷን ለማስፈታት የራሷን ህልሟን እንድትረሳው አስገድዷታል። ሊንዳ እውነቱን ለማጋለጥ የላምሮት ቤት ሰራተኛ ሆና በተቀጠረችበት ጊዜ ላይ አንዷየአይን ምስክር ውብዬንም አፈላልጋ አግኝታለች።

ሩሃማ እስርቤት በተሳሳተ ክስ ስለመግባቷ እና መሞቷ እውነቱ ሊጋለጥ በተቃረበበት ሰዓት ላይ ውብዬ ለጴጥሮስ በሚሰማት ስሜት ምክነያት ለሊንዳ የገባችላትን ቃል አጥፋለች። ይህ ምርጫዋ ግን የላምሮትን ቅናተኛነት በማነሳሳት ህይወቷ ያለጊዜው እንዲቀጭ አድርጓታል።

ላምሮት የሰውን ህይወት እንደፈለገች ማስወገድ ቀጥላለች፣ የሊንዳን ስለላ ብትደርስበት የሊንዳ ህይወት የሚተርፍ ይመስለዎታል? ሊንዳ ከጴጥሮስ ጋር መረጃ ለማግኘት የጀመረችው ግንኙነት ስትደርስበትስ?

ወይስ ከመያዟ በፊት ሊንዳ በአላት መረጃ የላምሮት እና ጴጥሮስን ወንጀል ታጋልጣለች?

አስተያየትዎን ያሳውቁን!

የተገፉት ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!