Logo

“እያየሁ ነው አትቀይሩት!” የሚያስብሉ ድራማዎች በአቦል ዱካ

ዜና
20 ማርች 2024
እነዚህን የአቦል ዱካ ድራማዎች በአቦል ዱካ ይጠብቋቸዋል!
abduka march 24 what to watch article

“እያየሁ ነው አትቀይሩት!” የሚያስብሉ ድራማዎች በአቦል ዱካ መቅረባቸውን ይቀጥላሉ። አቦል ዱካ ታይተው የማይጠገቡ ድራማዎችን ያቀርባል። ይህ ወርም አይለይም፤ ቻናሉ የተለያዩ አስገራሚ ድራማዎችንና ሪያሊቲ ትርኢቶች ያቀርባል።

አደይ

የአቦል ዱካ ተወዳጅ ድራማ “አደይ” ስድስተኛ እና የመጨረሻ ምዕራፉ ላይ ደርሷል። አቤል ባልታወቀ ሁኔታ ከቤት ሲጠፋ አደይ እና የአምዴ ቤተሰብ አጥብቀው ማፈላለጋቸውን ይጀምራሉ። ሜሮን የተባለችው የሥነ ልቦና ሐኪም ዋና ተጠርጣሪ በመሆኗ አቤልን ለማግኘት የሚደረገው የቤተሰብ ጥረት እንቅፋቶች ያጋጥሙታል። የተጠርጣሪዎቹ መሰወር ደግሞ ፖሊሶቹን ስራ ያወሳስበዋል። አቤል በመጨረሻ እንዴት ይገኝ ይሆን? አደይ ድራማን ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በ #አቦልዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይከታተሉት።

እንደ አንድ

አዲሱ በተወዳጅ ኮከቦች የተሞላው ምስጢራዊው ድራማ “እንደ አንድ” ልባችንን አንጠልጥሎታል። የምንወዳቸው ተዋናይ እታፈራው መብራቱ እና ሰለሞን ሙሄ በአዲሱ ድራማ ጥንዶች ሆነው ይቀርባሉ። ድራማው እታፈራው መብራቱ የምትጫወታትን ገጸ ባህሪ ፍቅርተን ታሪክ የሚከተል ነው። ፍቅርተ ፍጹም ህይወት የምትመራ የምትመስል ሴት ነች ነገር ግን ይህ ፍጹም ህይወት የደበቃቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ባለፉት ክፍሎች ፍቅርተ በከተማው ገንዘብ በመበተን የሚታወቀው ምስጢራዊ ቡድን አባል መሆኗን ተረድተናል። ነገር ግን ፍቅርተ እንዴት የእዚህ ቡድን አባል ልትሆን ቻለች? ምስጢሩን ለመፍታት #እንደአንድ ዘወትር ከሰኞ - አርብ 2:30 በ #አቦልዱካ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይከታተሉት።

አቦል ሚሊየነር

የአንድ ሚሊየን ብር ውድድሩ ይቀጥላል! ውድድሩ የሚካሄደው በሚያስደስት መልክ ሲሆን የሚያጓጉ ሽልማቶችን ይዞ ይቀርባል። እስከዚህ ዙር የደረሱት ተወዳዳሪዎች አንድ ሚሊየን ብሩን ለማሸነፍ የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው። ማን የአንድ ሚሊየን ብሩ አሸናፊ ይሆናል? ውድድሩን በ #አቦልሚሊየነር ዘወትር አርብ ከምሽቱ 1:30 በ #አቦልዱካ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይከታተሉት!

አቦል ዱካ እነዚህን እና የበለ የሚያዝናኑ ድራማዎችን ይዞ ማቅረቡን ይቀጥላል! ድራማዎቹ እንዳያመልጥዎ አቦል ዱካ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይከታተሉት! በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed