አደይ
አደይ ከሚያስጨንቋት ጉዳዮች ተሸሽጋ ቆይታ አሁን ወደ ቤት ተመልሳለች ነገር ግን አምዴ ቤት አዲስ እንግዶች ይጠብቋታል። የአቤል ወላጅ እናት ቤተሰብ በአምዴ ቤት መኖር ከጀመሩ በኋላ ብዙ ነገሮች እየተበላሹ ነው። የዚህም ምክንያት የአቤል ወላጅ እናት ሰሎሜ እና ባለቤቷ ሽመልስ ናቸው። ጥንዱ ለወ/ሮ ሮማን ያቀዱት በቀል ከአቶ ግርማ ጀምሯል፣ በቀጣይም በአደይ እና አቤል ያለውን ግንኙነት ለማበላሸት አስበዋል። ይህ የአምዴ ቤት ሌላ አዲስ አባል ሜሮንን የሚያካትት እቅድ ነው። ሜሮን ለአቤል ፍቅር ብላ ይሄን እቅድ ለመከተል ትስማማ ይሆን? አደይ ከእረፍቷ በኋላ የቤተሰቡን ችግር ለመፍታት ዝግጁ ትሆን?
አስኳላ
አስኳላ ትምህርት ቤት አዲስ አስተዳዳሪ ገብቷል። የበላቸው እንጀራ እናት ድርሻዬ አስኳላ ትምህርት ቤትን ወርሳ ትምህርትቤቱን ማስተዳደር ጀምራለች። የድርሻዬ ባህሪ ግን በላቸውን በጣም እያስጨነቀ ይገኛል። በተጨማሪም አቶ ክፍሌ የሶስተኛ ክፍል ተማሪ ፈተና ስለተሰጣቸው ወላጅ አምጥተው ተቃውሞ ያቀርባሉ። ይህ በአቶ ክፍሌ እና ኮዬ መሀል ጸብ ይፈጥራል። የአስኳላ ገጸ ባህሪያት በአዲሱ አመት እነዚህን አስቂኝ ጊዜያት እያሳለፉ ነው።
የባስሊቆስ ዕንባ
የብርሀን ቤተሰብ የደበቁት ምስጢር እየተፈታተናቸው ነው። ብርሀን ያደገችበት መንደር ዳባት ቤተሰቧን ለማግኘት እና ያልተመለሱላትን ከባድ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ትሄዳለች። ነገር ግን ስለቤተሰቧ የምትሰማው እና የምታምናቸው እውነቶች አንዳች የደበቁት እውነት እንዳላቸው እየተረዳች መጥታለች። ብርሀን ከወልጅ እናቷ ጋር እንደ እናት እና ልጅ መቀራረብ የምታደርገው ጥረት እየተሳካላት አይደለም። እናቷ ጠፍታ በቆየቻቸውን አመታት ውስጥ የተፈጠረ ነገር ጋር እነዲሚገናኝ ግልጽ ነው።
እነዚህን አጓጊ ታሪኮችን በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይከታተሉ!
እንኳን ለአዲስ አመት አደረሰዎ!