Logo

ጉድ ፈላ ምዕራፍ 2 በአቦል ቲቪ ሊጀምር ነው።

ዜና
26 ኖቬምበር 2021
የፍቅር ጦርነት::

ጉድ ፈላ ም ዕራፍ 2 በአቦል ቲቪ ኀዳር 17 አርብ ከምሽቱ 3፡30 ይጀምራል:: ይህ አስቂኝ ድራማ ስለይትባረክ እና አባቱ ሀይሉ ያላቸውን የኑሮ ልዩነት ያሳያል።

ባለፈው ምዕራፍ ላይ ይትባረክ በእምነትን እንደሚወዳት ሊገልፅላት ሲታገል ቆይቷል። ሴቶችን የማናገር ፍራቻው እንቅፋት ሆኖበታል። በተቃራኒው አባቱ ሀይሉ ሴቶችን በቀላሉ ማናግር በመቻሉ እናም ጊዜውን ከተለያዩ ሴቶች ጋር ያሳልፋል።

ሀይሉ ግን በእምነትን በእምነትን በመውደዱ የይትባረክን ደካማ ጎን ተጠቅሞ ሊቀርባት ይሞክራል። በእምነት መ/ቤት ውስጥ ይትባረክን ለማናገር ሞክራለች።

ከአባት እና ልጅ ማን በእምነትን በፍቅር የሚያሸንፍ ይመስለዎታል?

ማን ይመቸዎታል? ኮመንት በማድረግ ያሳውቁን!

ጉድ ፈላ ዘወትር ዓርብ ከምሽቱ 3:30 በአቦል ቲቪ ይከታተሉ!