Logo
Tilla Slim Billboard 1600x600 copy
channel logo

Tilla

465DramaPG13

በሀጥያት እና ጥላቻ የተሳሰረ ትዳር - ጥላ

ዜና
28 ጁላይ 2023
የጫካ እና ዙፋን ትዳር ከፍቅር በተቃራኒ የተመሰረተ ነው፣ ይሄን እውነታ እንዴት ቤተሰባቸው ላይ ተጽእኖ አሳድሯል?
tilla article

ጫካ እና ዙፋን በቤተሰባቸው ባላቸው ግዴታ ምክንያት ትዳር መስርተዋል። ይህ ትዳር ከመጀመሪያው ጀምሮ በጥላቻ እና ቁጭት እንዲሞላ ያደረገው ታሪክ ሰላም እንዳይኖራቸው አድርጓቸዋል።

ጫካ ሚስቱ መድሀኒት እና ልጁ ፍኖትን ለመጠበቅ ሲል ንብረቱን የራሳቸው ለማድረግ የሚጥሩት ቤተሰብ ጋር ጸብ ውስጥ ይገባል። የዚህ ቤተሰብ አባል የሆነችው ዙፋን፣ ጫካ እና መድሀኒት ከልጃቸው ጋር እንዲያመልጡ ለመርዳት ትሞክራለች። ነገር ግን በዚህ ጦርነት መሀል የወንድሞቿ ህይወት ሲቀጭ ለጫካ የምታደርገው እርዳታ ይቆማል። በመጨረሻ ጫካ መድሀኒትን የሚያስገድል ትልቅ ምርጫ ሲቀርብለት፣ ዙፋን ለዘላለም የምቆጨውን ምርጫ እንዲመርጥ ትመክረዋለች።

ዙፋን እና ጫካ ለቤተሰባቸው ጉዳት ካሳቸው ትዳራቸው ነበር። በመካከላቸው የተፈጠረውን እያደረ የሚሰፋ ጥላቻ ያለውን ክፍተት ያስፋፋዋል። ጫካ ለመጀመሪያ ልጁ ፍኖት ብቻ የሚሰጠው ልዩ ትኩረት ዙፋንን አስቀንቶ፣ ጥላቻዋ ለፍኖትም እንዲተርፍ አድርጎታል።

የጫካ እና ዙፋን አለመግባባት ትዳራቸውን ብቻ ሳይሆን የልጆቻቸውን ግንኙነት በቅናት የተሞላ አድርጎታል። ይሄ በጥላቻ የተሞላ ትዳር በመጨረሻ ቤተሰቡን ለሁለት ከፍሎ ሽጉጥ እርስ በራስ ላይ እንዲደቅኑ አድርጓቸዋል። የጫካ እና ዙፋን መጨረሻ ምን ይሆን? ፍላጎታቸውን በማሳወቅ ቤተሰባቸውን ከጨመሩበት ገደል አፋፍ መውጣት ይችሉ ይሆን?

መጨረሻቸውን በጥላ አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይከታተሉ!