Logo
Afaf S1

የአፋፍ ተወዳጅዎች ተዋንያን ከሰይፉ ጋር በኢቢኤስ ቆይታ ያደርጋሉ

ዜና
07 ጁላይ 2023
የአፋፍ ተዋንያን ቆይታ ይመልከቱ።
afaf interview article

የአቦል ቲቪ አዲሱ ቴሌኖቬላ ሰኔ 19 ከምሽቱ 2፡00 ጀምሯል። ድራማው የሚያጠነጥነው በ 1984 ዓ.ም የዙማ መንደርን የመቀየር ህልም በታጠቁ ሁለት ጓደኛሞች ታሪክ ነው፡፡ ሁለቱ ወጣቶች ከእለታት በአንዱ ቀን ሰው ዝር በማይልበት ግዙፍ ተራራ ዙሪያ ሲሯሯጡ ድንገት አንድ በጣም ውድ ማዕድን ያገናኛሉ፡፡

ይህ ልብ አንጠልጣይ ድራማ ተወዳጅ ተዋንያን መዐዛ ታከለ፣ ነብዩ ባዬ፣ ተፈሪ አለሙ፣ ሚካኤል ሚሊዮን እና ሌሎች ማራኪ ተዋንያን ይዞ ቀርቧል። ከዚህም አልፎ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊ ራሱን የቻለ የቀረፃ መንደር በመገንባት ፕሮዳክሽኑን እያከናወነ የሚገኝ ልብ አንጠልጣይ ቴሌኖቬላ ነው፡፡

ስለ አፋፍ ይበልጥ ለማወቅ ተዋንያን መዐዛ ታከለ፣ ነብዩ ባዬ፣ ተፈሪ አለሙ እና ሚካኤል ሚሊዮን ከሰይፉ ጋር በኢቢኤስ ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ፡

ክፍል 1

ክፍል 2

አፋፍ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!