Logo
Adey S4 Slim Billboard Desktop

አስደናቂ ጥንዶች – አደይ

ዜና
14 ፌብሩወሪ 2022
በፍቅራቸው ለየት ያሉ ጥንዶች።

በአቦል ቲቪ የሚቀርበው ተወዳጁ አደይ ድራማ ብዙ አስደናቂ ገፀ ባህሪያት ይዞ ይቀርባል። በእነዚህ ገፀ ባህሪያት ውስጥ ብዙ አይነት የፍቅር ግንኙነቶች ተፈጥረዋል ፡፡ ስለዚህ የዘንድሮውን የፍቅረኛሞች ቀን በማስመልከት እነዚህ ልዩ ጥንዶች ማን ማን እንደነበሩ እንመለከታለን።

1. አቤል እና አደይ

በብዙ ውጣ ውረድ የተሞላው የአደይ እና አቤል ፍቅር የጀመረው አደይ በሰራተኝነት አምዴ ቤት ስትቀጠር ነበር። አደይ እና አቤል በመሀላቸው በተደጋጋሚ የሚፈጠረው አለመግባባት አብረው እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል።

2. ሁንአንተ እና አደይ

ሁንአንተ ከአደይ ጋር በስራ ምክንያት የጀመረው ግንኙነት ወደ ፍቅር ሲቀየር ተመልክተናል። አደይ ከአምዴ ቤት ተባራ ሁንአንተ ጋር መስራት በጀመረችበት ጊዜ ለአቤል ያላትን ፍቅር አልረሳችውም። ሁንአንተ ግን ለአደይ የነበረውን ፍቅር ለማሳወቅ ወደኋላ ባለማለቱ ግንኙነታቸው ወደ ጋብቻ አምርቷል። ነገር ግን የአደይ እና ሁንአንተ ጋብቻም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት አልዘለቀም።

3. ምዕራፍ እና ዳኜ

ከአደይ ጋር ያነበረው ግንኙነት ባለመሳካቱ እራሱን ወደ ዳኜ ቀይሮ ሁንአንተ የጀመረው አዲስ ግንኙነት ብዙ ውጣውረድ ነበረው። የዳኜ እና ምዕራፍ ታሪክ የተመሰረተው በውሸት ቢሆንም ምዕራፍ ለዳኜ የሚሰማት ፍቅር እውነተኛ ነበር። ለዚህም ነው ዳኜ ማንነቱን ረስቶ ሲነቃ ምዕራፍ እውነተኛ ግንኙነት ለመመስረት የነበራት ተስፋ መቋጨቱ ተመልካችን ያሳዘነው።

4. ራሄል እና አሹ

ራሄል ከቤተሰቧ ጋር በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት የመረሳት ስሜት ሲሰማት በነበረበት ወቅት ላይ አሹን ተዋወቀችው። በትንሽ ጊዜ ውስጥ ራሄል እና አሹ በፍቅር ወድቁ። አሹ ከራሄል አጠገብ ቆሞ በተደጋጋሚ ሲደግፋት ስለ መረሳትዋ ያላት ስሜት ጠፋ። እነዚህ ጥንዶች እርስ በእርሳቸው ያላቸው ድጋፍ እና ፍቅር የተመልካችን ልብ ይነካል።

5. ማክዳ እና እያሱ

የማኪ እና እያሱ ጋብቻ በአካባቢያቸው ላለው ሰው ችግር የሚፈጥር እና ለራሳቸው ጥቅም ብቻ የሚያቅዱ ጥንድ መሆናቸውን አናቃለን። ግን እያሱ ለማኪ የነበረው ፍቅር እስዋ የምትፈልገውን ነገር በጠቅላላ እንድታገኝ ምንም ከማድረግ እንደማያስቆመው አይተናል። በመሃላቸው የነበረው ፍቅር የተመሰረተው በሥሥት እና በምኞት ከመሆኑ የተነሳ መጨረሻቸውም የማያምር ሆነ።

6. ዝናሽ እና አቶ ታደሰ

ዝናሽ እና አቶ ታደሰ አስቂኝ እና የመቻቻል ፍቅር አላቸው። ነገር ግን ዝናሽ ከድህነት ለመውጣት የምታደርገው ጥረት አቶ ታደሰ የማያምኑበት መንገድ በመሆኑ በመሀላቸው ብዙ ጸብ ተፈጥሯል። በዚህ እና በመሳሰሉ ሌሎች ብዙ ነገሮች ባይግባቡም የአቶ ታደሰ እና ዝናሽ ፍቅር ሁሌ ለቤተሰባቸው ከምንም በላይ ቅድሚያ እንዲሰጡ አድርጓቸዋል።

7. ወ/ሮ ሮማን እና አቶ ግርማ

ወ/ሮ ሮማን በተደጋጋሚ የሚጎዱት በአቶ ግርማ ስህተት ቢሆንም ለልጆቻቸው ያላቸው ፍቅር ከአቶ ግርማ እንዳይለያዩ ያደርጋቸዋል። የአቶ ግርማ እና ወ/ሮ ሮማን ፍቅር የጀመረው በጥሩ ሁኔታ ቢሆንም አብረው ሲቀጥሉ  በመሀላቸው የነበረው የሚስጥር ብዛት ጋብቻቸው የጀመረበትን አይነት ፍቅር እንዳይኖረው አድርጓል።

 

Adey S4 Poll BG
አደይ – የፍቅረኛሞች ቀን

ከእነዚህ የአደይ ድራማ ጥንዶች ማንን ይወዳሉ?

አደይ እና አቤል67%
አደይ እና ሁንአንተ7%
ምዕራፍ እና ዳኜ0%
ማክዳ እና እያሱ10%
ዝናሽ እና አቶ ታደሰ10%
ወሮ/ ሮማን እና አቶ ግርማ7%

አደይ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!