Logo
Adey S4 Slim Billboard Desktop

ከአደይ ነጠላ ዜማ ኮምፖዘር እስራኤል መስፍን ጋር ቃለ- መጠይቅ - አደይ

ዜና
26 ጃንዩወሪ 2022
ስለነጠላ ዜማው አሰራር እንረዳለን።

ከአደይ ድራማ ነጠላ ዜማ ኮምፖዘር እስራኤል መስፍን ጋር ስለተወዳጁ የአደይ ድራማ አጃቢ ነጠላ ዜማው ጥያቄና መልስ አድርገናል። ስለነጠላ ዜማው አሰራር ለማወቅ ማንበብ ይቀጥሉ።

  1. ለአደይ ድራማ ሙዚቃ ለማቀናበር ከታሪኩ ውስጥ ምን አነሳሳህ ?

ብዙ ጊዜ የፊልም ማጀቢያዎችን ስሰራ ራሴን የምገልፅበት እና ሁሉም ቦታ ተዳራሽ የሆነ ድንበር ተሻጋሪ ስራ ስጠብቅ ነበረ። እናም አደይ የተሻለ እና በ DS tv ድንበር የሚሻገር በታሪኩም የተሟላ ሆኖ ሳገኘው የበለጠ ራሴን እገልፅበታለሁ አልኩና ተነሳሳሁ። 

  1. ተመልካቾች ሙዚቃውን ሲያዳምጡ ምን አይነት ስሜት እንዲሰማቸው ትፈልጋለህ?

ሃገርኛ ስራ እንደመሆኑ መጠን የአደይ ተመልካች ራሱን ታሪኩ ውስጥ እንዲያገኘው አይነት ስሜት መስጠት እፈልጋለሁ።

  1. ሙዚቃውን በምታቀናብርበት ወቅት ያጋጠመህ እንቅፋት ነበር?

    አዎን የመጀመሪዎቹ ኤፒሶዶች ላይ የቴሌኖቬላውን አካሄድ በደምብ እስክላመደው ውስን እንቅፋቶች ነበሩብኝ በኋላ ላይ ግን ራሴን ከስራው ጋር በማዋሃድ እና የስራው አንድ አካል(ቤተሰብ) በማድረግ ቀርፌዋለሁ። ለዚህም ሰው መሆንን ሶሚክ ላመሰግነው እወዳለሁ። 

  1. ሙዚቃው ምን ያህል ተወዶልኛል ብለህ ታስባለህ ?

በመጀመሪያ ለአደይ ቴሌኖቬላ መስጠት አለብኝ ብዬ ያሰብኩትን ቀለም ሰጥቻለሁ ብዬ አስባለሁ በመቀጠል ከምሰማቸው ፊድባኮች ተወዶልኛል ብዬ አስባለሁ።

  1. ነጠላ ዜማውን የት እና በምን መልኩ አግኝተን ማድመጥ እንችላለን ?

የአደይ ማጀቢያ ሙዚቃዎችን በየሲዝኑ መዝጊያ በነጠላ ዜማ መልክ ሰርተናቸዋል እጃችን ላይም እየሰራነው ያሉ የአደይ ቴሌኖቬላ ነጠላ ዘፈኖች አሉ የመጀመሪያውን ማጀቢያ ዜማ You Tube ላይ አለ።

የአደይን ማጀቢያ እዚህ ያድምጡ!

አደይ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!