Logo
Adey S4 Slim Billboard Desktop

የአደይ አዲሱ ምዕራፍ – አደይ

ዜና
07 ጃንዩወሪ 2022
በአደይ ምዕራፍ 4 ላይ መጠበቅ የምንችላቸው።

አደይ ምዕራፍ 3 በልብ አንጠልጣይ መንገድ ተጠናቋል። አቤል አደይ የታገተችበትን ቦታ ከምዕራፍ ጋር አግኝቶታል ግን ከዳኜ ጋር በገጠመው ጸብ ምክነያት የአደይ ህይወት አደጋ ውስጥ ይገባል። ይህ ዳኜ ማንነቱን እንዲያስታውስ እና ሁንአንተ መሆኑን እንዲያምን አስገድዶታል። ግን ይህ ሁንአንተን ከፖሊስ እጅ እና አደጋ ውስጥ አላወጣውም። ከፖሊስ ሊያመልጥ ሲሞክር ከደረሰበት ጉዳት ድኖ ሆስፒታል ሲነቃ የዳኜን ማንነት መርሳቱን ተረድተናል።

ምዕራፍ 4 እነዚህን አጋጣሚዎች ይዞ መጥቷል፣ አቤል በወ/ሮ ሮማን እናቱን የመፈለግ እቅድ በማዘኑ መጠጥ ማብዛቱ፣ አደይ የምትወደውን ስራ በአዲስ መንገድ መቀጠሏን እና ምዕራፍ በዳኜ መርሳት መጎዳትዋን። ስለዚህም እኛ ያለን ትልቁ ጥያቄ ስለሁንአንተ ነው።

ሁንአንተ የት ነው ያለው? ዳኜ ሆኖ ያደረገውን ሁሉ መርሳቱ እውነት ይሆን? ራሄል እና አሹ ለምዕራፍ መከፋት በማዘናቸው የሁንአንተ መርሳት እውነት መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረት ምን አይነት መልስ የሚያመጣ ይመስለዎታል?

አደይ እና ሁንአንተ በመጨረሻ መታረቅ ይችሉ ይሆን? ወይስ አደይ ከአቤል ያላትን የልጅነት ፍቅር መርሳት ያቅጣታል? ሰሞኑን በተመለከትናቸው አዳዲስ ክፍሎች የአደይ የልጅነት ጓደኛዋ ታሪኩ ለእሷ የፍቅር ስሜት እንደሚሰማው ተረድተናል፣ አደይ ስሜቱን የምትጋራ ይመስለዎታል?

አስተያትውን ኮመንት በማድረግ ያሳውቁን!

Adey Poll BG
አደይ

ማንን ይመርጣሉ?

አደይ እና ሁኔ43%
አደይ እና አቤል36%
አደይ እና ታሪኩ21%

አደይ ከሰኞ - እርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!