Logo
Askuala S2

ስለአስቂኙ አስኳላ ድራማ ተዋናይ ማማሩ ተስፋ - አስኳላ

ዜና
20 ኦክቶበር 2021
ስለማማሩ ተስፋ የተረዳናቸው አንዳንድ ነገሮች።

ባለፈው ሳምንት ዓርብ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ከማማሩ ተስፋ ጋር የመጨረሻው የአስኳላ ተዋናይ ፌስቡክ ላይቭ ቀርቧል። ስለተወዳጁ ተዋናይ ማማሩ ተስፋ የተረዳናቸው አንዳንድ ነገሮች እነዚህ ናቸው፡

1. ተዋናይ ለመሆን ምን አነሳሳህ ?

ለረጅም ጊዜ ተዋናይ ለመሆን ፍላጎት ነበረው። ማማሩ ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ በትምህርት ቤት እና ያደገበት አካባቢ የተለያዩ ድራማዎች ላይ ተሳትፏል። በዚህ ወቅት ስነጽሁፍ የሱ ተሰጥኦ መሆኑን ለይቶ አውቋል። ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ የቲያትር ትምህርት ማጥናት ወደ ትወና እና ፊልም ፕሮዳክሽን እንዲጠጋ እድል ሰጥቶታል።

2. እስከአሁን ከሰራሃቸው ስራዎች ውስጥ ትረካ ይገኝበታል?

ማማሩ ተወልዶ ያደገባት ሞጣ የምትባል ከተማ ውስጥ ያለው ብቸኛ የመዝናኛ ምንጭ ሬዲዮ ነበር። ተማሪ ሆኖ ሬዲዮ እየሰማ ነበር ያደገው። ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮም የሬዲዮ ትረካዎች እና ድርማዎችን ለኢትዮጵያ ሬዲዮ በማቅረብ ተሳትፎ ያደርግ ነበር። ብዙ ተመልካቾች በዚህ ስራው እንደሚያስታውሱትም ይናገራል።

Poll Question Desktop 1600 x 254
አስኳላ ላይቭ ቻት

የማማሩን ቅድሚያ ስራዎች ያውቋቸዋል?

አዎ64%
አይ36%

3. ለአስኳላ ድራማ ተመልካቾች ወይም ለአድናቂዎችህ ምን ማለት ትፈልጋለህ?

የአስኳላ ተመልካቾች እና አድርናቂዎቹን እጅግ አመስግንዋል። ወደፊት ለረጅም ጊዜ ከአስኳላ ድራማ ጋር ተመልካቾች አብረው እንዲዘልቁ ጠይቋል።

በተጨማሪም ምስጋናውን በአስኳላ ድራማ ላይ ተሳትፎ እንዲያደርግ እድል ለሰጠው ዳይሬክተር እና ደራሲ በኃይሉ ዋሴ እና ብዙ ተሰጥኦ ላላቸው ሰዎች እድል ይዞ ለቀረበው አቦል ቲቪ አቅርቧል።

የማማሩ ፌስብክ ላይቭ ካመለጠዎ ሊንኩን በመጫን ይመልከቱ!

 

Posted by Abol TV on Friday, 15 October 2021

አስኳላ ድርማ ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ ይከታተሉ!