Logo
Askuala S2

የዘላለም ምጽላል ቆይታ በፌስቡክ ላይቭ - አስኳላ

ዜና
13 ኦክቶበር 2021
ስለተወዳጁ የአስኳላ ስፖርት አስተማሪ ማእበል ተዋናይ ዘላለም በፌስቡክ ላይቭ የተረዳናቸው አንዳንድ ነገሮች።

ባለፈው ሳምንት በአቦል ቲቪ ፌስቡክ ላይቭ የአስኳላ ተወዳጅ ተዋናይ ዘላለም ቀርቦ ነበር። በቆይታው ጊዜ ስለራሱ እና ስለአስኳላ አጫውቶን ነበር። ስለዘላለም ምጽላል አዳዲስ የተረዳናቸ ነገሮች እነዚህ ናቸው፡

ተዋናይ ለመሆን ምን አነሳሳህ?

ከልጅነቱ ጀምሮ ለአርት እና ፊልም የነበረው አድናቆት ዩኒቨርስቲ ሲገባ ቲያትርም አንዲማር አነሳስቶታል። የትወና ስራ መስራት ትችላለህ ብለው የነገሩት ተሻለ አሰፋ እና የአስኳላ ዳይሬክተር እና ደራሲ በሀይሉ ዋሴ ነበሩ።

ተዋናይ ባትሆን ምን ሙያ ላይ እሰማራለሁ ብለህ ታምናለህ?

ዩኒቨርስቲ ከመግባቱ በፊት ኳስ ተጫዋች መሆን ይፈልግ እንደነበር አጫውቶናል።

ከዩኒቨርስቲ በኋላ ልክ በአስኳላ  ድራማ እንደሚጫወተው ገጸ-ባህሪ ማእበል አስተማሪ የመሆን ፍላጎት ያደርጋል።

ለአስኳላ ድራማ ተመልካቾች ወይም ለአድናቂዎችህ ምን ማለት ትፈልጋለህ?

አስኳላ ድራማ ከመዝናናት እና ከማሳቅ አልፎ ለማስተማር የተዘጋጀ ኮሜዲ ሲሆን ሀሳቡን ተመልካቾች እንደወደዱት ተስፋ አለው።

የዘላለም ፌስብክ ላይቭ ካመለጠዎ ሊንኩን በመጫን ይመልከቱ!

 

Posted by Abol TV on Friday, 8 October 2021

በዚህ ሳምንት ዓርብ የአቦል ቲቪ ፊስቡክ ላይቭ ከማማሩ ተስፋ ጋር ከምሽቱ 1፡00 ይከታተሉት!