Logo

የኔታ እና ሳይንስ ትምህርት - አስኳላ

ዜና
28 ጁላይ 2021
አዝናኝ ተቃውሞ ከየኔታ ጋር።

የኔታ አስኳላ ትምህርት ቤት ከተመዘገቡ  አምስት ወር ሆኗቸዋል። በዚህ ጊዜ የኔታ ከተማሪዎች እና አስተማሪዎች ጋር የነበራቸው ግንኙነት በጣም አስቂኝ እና አዝናኝ ነበር።

እስካሁን ካሳለፉት ጊዜያት በጣም አስቂኝ የምንላቸው እነዚህ ናቸው፤ የኔታ እና የእርሻ ትምህርታቸው፣ የአስኳላ ሰላይ የኔታ እና የአስተማሪዎች አራሚ የኔታ።

በዚህ ጊዜያቶች ግን የኔታ የሳይንስ ክፍል በመቃወም ክፍል ሲረብሹ አይተን አናውቅም። አሁን ግን ስለ እንስሳ እና ሰው ተቀራራቢነት የሚማሩት ትምህርት አልተዋጠላቸውም።

ስለዚህ ርእስ ምን ያድርጉ ይሆን? ተቀብለው ያልፉታል ወይስ እንደተለመደው ሀሳባችውን ይሰጡ ይሆን?

ይሄን ለማየት አስኳላ ኮሜዲ ድራማን ይከታተሉ!

አስኳላ ረቡዕ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይተላለፋል።