Logo

ከአስኳላ ድራማ ውስጥ የማይረሱ ጊዜያቶች - አስኳላ

ዜና
10 ኦገስት 2021
አምስት የማይረሱ ጊዜያት።

ተወዳጁ የአቦል ቲቪ ድራማ አስኳላ ምዕራፍ 1 ተጠናቋል። ይህ አስቂኝ ድራማ የተለያዩ የማይረሱና አስደሳች ጊዜያቶችን ይዞ ቀርቧል።

ከአስኳላ አስቂኝ ድራማ በጣም የወደድናቸው አምስት ጊዜያቶች እነዚህ ናቸው፤

1. የኔታ የእንግሊዘኛ ፊደሎች አይዋጥላቸውም።

በእንግሊዘኛ ክፍል ውስጥ ስለሚዋጡ ፊደላት ሲማሩ ስለፊደላቱ አስፈላጊነት ከአስተማሪዋ ጋር በመከራከራቸው የተፈጠረው ረብሻ ለተመልካች በጣም አዝናኝ ጊዜ ነበር።

2. የኔታ የእርሻ ክፍል ጀምረዋል።

የአስኳላ ተማሪዎች ስለእርሻ እየተማሩ እንዳልሆነ ሲረዱ የኔታ የራሳቸውን ክፍል ማስተማር ይወስናሉ። ስለዚህ ክፍል ዳይሬክተር በላቸው ሲደርስበት የኔታ ለማስተማር እየተጠቀሙበት የነበረውን ዶማ የጦርነት መሳሪያ ነው በማለት የእርሻ ክፍሉን ያስቆማሉ።

3. የአስኳላ አስተማሪዎች ፈተና።

አስኳላ ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ስራ ብቃት በሚገመገምበት ወቅት ላይ የኔታ በክፍል ሰዓት መመለስ የማይችሉትን ጥያቄ እንዳይጠይቁ የአስኳላ አስተማሪዎች ያደረጉት ጥረት በጣም አዝናኝ ነበር።

4. የኔታ ሰላይ ናቸው።

የኔታ የአስኳላ ህግ ስላልተዋጠላቸው መቃወም ሲጀምሩ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር በላቸው የኔታ አስኳላን ሊበጠብጡ የመጡ ሰላይ ናቸው ብሎ ያምናል። ስለዚህም የየኔታን እውነተኛ እቅድ ለማግኘት ከአማርኛ አስተማሪ ይነበብ ጋር መረጃ ለማሰባሰብ ይነሳል።

5. ጥንዶቹ አብረው ሊማሩ ነው።

እስካሁን ባለፉት ጊዜያት የኔታ አስኳላ ትምህርት ቤት ከልጆች ጋር ሲማሩ ቆይተዋል፣ አሁን ግን ባለቤታቸው እምወድሽ አብረው መማር ይፈልጋሉ። ይሄንን የኔታ ስለሚቃወሙ ዳይሬክተሩን ምዝገባው እንደማይቻል ለማረጋገጥ ሲሄዱ አለመፈለጋቸውን ሲረዳ በላቸው ከትምህርት ቤቱ የኔታን ለማስወጣት ለምዝገባው ፈቅዷል።

በሚቀይጥለው ምዕራፍ የኔታ ከባለቤታቸው ጋር አስኳላ ትምህርት ቤት መማር ይጀምሩ ይሆን?

የሚወዱት የአስኳላ አስቂኝ ጊዜ የትኛው ክፍል እንደሆነ ይንገሩን!