Logo
Nafikot S2

በቀል - ናፍቆት

ዜና
01 ኦክቶበር 2021
የናፍቆት ምዕራፍ 2 ጀምሯል።

ናፍቆት ሙዚቃዊ ድራማ ስለ ገላ የተባለች ድምጻዊ እና ልጆቿ የተወሳሰበ ግንኙነት ነው።

ባለፈው ምዕራፍ ግሩም ለፀሀይ ባለው ፍቅር ምክንያት ምንም ከማድረግ ወደኋላ እንደማይል ተረድተናል። በአዲሱ የናፍቆት ምዕራፍ 2 ክፍል ላይ ቃልአብ የባዳድ ሞት ላይ የግሩም እጅ እንዳለበት ተረድቷል። ቃልአብ ከግሩም ጀምሮ ማንንም ሳይምር የባዳድን ሞት ለመበቀል ተዘጋጅቷል። የወንድማማቾቹ ፀብ ለፀሀይ ፍቅር ከመወዳደር አልፏል።

ፀሀይ ግሩምን መርሳት አልቻለችም ግን የእናቷን ቃል ማክበር ትፈልጋለች፣ የጋለው ስሜቷ ወደ ግሩም ይመልሳት ይሆን? ገላ ቤት ውስጥ ባለመኖሯ ሰናይት ልጆቿን ማስፈራራት ቀጥላለች። ልሳን ይህ አላስችል ብሏታል፣ ንዴቷ ከሰናይት ጋር ያጣላይት ይሆን? ወይስ ለገላ ስትል ከሰናይት ጋር ፀብ ውስጥ ላለመግባት ትሞክራለች?

በፀጋው በወንድሙ መፈታት ባለው ደስታ ምክንያት ያለውን ብር ስጦታ ላይ እያጠፋው ነው። ይህ ባህሪው ከቀጠለ እሱ እና ወንድሙ የት ይደርሱ ይሆን? ይህ ደስታ የሚቀጥል ይመስልዎታል?

በአዲሱ የናፍቆት ምዕራፍ ውስጥ ድራማው እየጋለ እና ገጸ-ባህሪቹ ፈተናቸው እየጨመረ ነው። የትኛውን የናፍቆት ገጸ-ባህሪ እንደሚያደንቁ ያሳውቁን!

አዳዲስ ክፍሎች እንዳያመልጥዎ ማክሰኞ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!