Logo
Adey S3

ሁንአንተ ወይስ ዳኜ? - አደይ

ዜና
17 ኖቬምበር 2021
የሁለት ተኩላ ትግል።

አንድ ታዋቂ ቼሮኪ አፈ ታሪክ ስለማንነት የሚያቀርበው የስነ ልቦና ጥያቄ በአደይ ላይ ስለምንመለከተው የሁንአንተ (ዳኜ) ገጸ-ባህሪ ያስረዳናል ። አፈ ታሪኩ በአንድ አዛውንት እና የልጅ ልጃቸው መካከል ስለነበረው ውይይት ነው።

አዛውንቱ ለልጅ ልጃቸው በሰው ውስጥ ሁሌም ጦርነት ላይ ሆነው ስለሚኖሩት ተኩላዎች ይነግሩታል። አንደኛው ተኩላ ክፋተኝነትን ወክሎ የሚዋጋ ሲሆን፣ ሁለተኛው ተኩላ ደግሞ መልካምነትን ወክሎ የሚዋጋ ነው። ልጁ አያቱን የትኛው ተኩላ እንደሚያሸንፍ ሲጠይቃቸው “የምትመግበው ተኩላ።” ብለው መለሱለት።

በአደይ ድራማ ውስጥ የሚቀርበው የሁንአንተ ገጸ-ባህሪ በምዕራፍ 2 ላይ የሚመግበው መልካሙን ተኩላ ነበር። ግን በአደይ እና አቤል ግንኙነት ምክንያት የፈጠረበት የመበደል ስሜት እራሱን ወደ ዳኜ ቀይሮ እንዲቀርብ አድርጎታል። የዳኜ ገጸ-ባህሪ ክፉ እና ቅናተኛው ተኩላን እየመገበው መሆኑን ተረድተናል።

ይሄን በሁንአንተ እና ዳኜ መካከል ያለው የአዕምሮ ትግል በተደጋጋሚ ተመልክተናል። በሚቀጥሉት የአደይ ክፍሎች የትኛውን ገጸ-ባህሪ የምንመለከት ይመስለዎታል? ማሬዋ የጠቆመቻቸው ጥፋቶች ሁንአንተን ወደራሱ ይመልሱት ይሆን?

ስለሁንአንተ ገጸ-ባህሪ ምን እንደሚያስቡ ኮመንት በማድረግ ያሳውቁን!

አደይ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ 146 ከምሽቱ 8፡00 ይተላለፋል።