channel logo
Gizat S1

የአቦል ቲቪ ቆፍጣኖችና እና ባለራዕዮች፡ መልካም ዓለም አቀፍ የወንዶች ቀን!

ዜና20 ኖቬምበር 2025
የዓለም አቀፍ የወንዶች ቀን በትናንትናው እለት ተከብሯል! ይህ ቀን ለወንዶች ስኬት፣ ታማኝነት እና ውስብስብ የሕይወት ትግል እውቅና የምንሰጥበት ነው።
abol november article

የዓለም አቀፍ የወንዶች ቀን በትናንትናው እለት ተከብሯል! ይህ ቀን ለወንዶች ስኬት፣ ታማኝነት እና ውስብስብ የሕይወት ትግል እውቅና የምንሰጥበት ነው።

ከሥልጣን ጥማት እስከ ፍትህ ፍለጋ፣ ከታማኝነት ውሳኔ እስከ ቤተሰብ ፍቅር ድረስ የአቦል ቲቪ የወንድ ገጸ-ባህሪያት አሸናፊዎች ብቻ ሳይሆኑ እውነተኛ የሰው ልጅ ስሜትና ውጣ ውረድ ተሸካሚዎች ናቸው። ከእነዚህ መካከል አራት ቁልፍ ገጸ-ባህሪያትን እንመልከት!

1. ሰመረ (ከ"ግዛት" ድራማ)፡ የወንጀል መሪ በለስላሳ ልብ!

ሰመረ በ"ግዛት" ድራማ ላይ ባለውስብስብ ባህሪና ስልጣንን በጉልበት ለመጨበጥ የሚፈልግ ቁጡ ገጸ-ባህሪ ነው። የአባቱን የወንጀል ግዛት ለመምራት ያለው ፍላጎት ከማንም በላይ ነው! ሆኖም፣ ይህ ግትርነት በቤተሰቡ ፍቅር ይለሰልሳል።

ሰመረ የእንጀራ እናቱ እና ግማሽ ወንድም/እህቶቹ በሙሉ ልብ እንዲቀበሉት በከፍተኛ ሁኔታ ይፈልጋል። የቤተሰቡ ራስ ለመሆን የሚያደርገው ጥረት የኃላፊነት ስሜትን እና የስልጣን ጥማቱን ያጋጫል። ሥልጣን ወይስ ቤተሰብ? የሰመረ ታሪክ ምንጊዜም ግጭቶች ናቸው።

2. አቤል (ከ"ግርድ" ድራማ)፡ ለታማኝነት የኖረ ባለውለታ!

አቤል፣ የ"ግርድ" ዋና ገጸባህርይ ሲሆነ፣ በምርምር ባልደረቦቹ ክህደት የመግደል ሙከራ ደርሶበት፣ ሞቷል ተብሎ ታምኖ ለሃያ ዓመታት ተሰውሮ የኖረ ሰው ነው። ለዚህ ሁሉ የዳረገው የመርምሩን ውጤት ለባዳ አልሸጥም ማለቱና ሀገሩን አሳልፎ አለመስጠቱ ነው። ለፍትህ ጥያቄው እና ትቶት የሄደውን ቤተስብ ፍለጋ ወደ ከተማ ተመልሷል።

አቤል የመሰዋዕትነትን ዋጋ የከፈለ፣ ፍትህን ለማግኘትና ጠላቶቹን ለማቆም የተመለሰ ቆራጥ ሰው ነው!

3. አካ ቦቹ (ከ"ባሻገር" ድራማ)  የፍትህና እና ያጣውን የማስመለስ ትግል!

አካ ቦቹ፣ የ"ባሻገር" ጀግና። በሐሰት የግድያ ወንጀል ተከሶ፣ ነፍሰ ጡር ሚስቱን ትቶ ስምንት ዓመታት ሙሉ ተሰውሮ ኖሯል። ዛሬ ተመልሶ ንጹህነቱን ለማረጋገጥ እና የናፈቀውን ቤተሰቡን ለማግኘት እየታገለ ነው። ያኔ በሀሰት ያስወነጀሉት ጠላቶቹ አሁንም እሱን ከማሳደድ አላረፉም።

አካ ቦቹ ግን ሀቅን ሰንቆ  አለመሸነፍን መርጧል! የእሱ ታሪክ የጠፋውን መልሶ ለማግኘት የሚደረግ የቁርጠኝነት ማሳያ ነው።

4. ሙሌ (ከ"ያልተዳኘ ህሊና”)፡ ታማኝነት እስከ መስዋዕትነት!

ሙሌ፣ ከ"ያልተዳኘ ህሊና" ድራማ፣ ለጓደኝነት እና ለቤተሰብ ጥብቅ ፍቅር ያለው እና በውሳኔዎቹ የሚጸና ሰው ነው። በአንድ መጥፎ አጋጣሚ በተፈጠረ የግድያ ወንጀል ውስጥ እራሳቸውን ያገኙት ሙሌ እና ጓደኞቹ እውነቱን በማውጣትና እራሳቸውን በመጠበቅ መሀል ከባድ ውጥረት ውስጥ ቆይተዋል።

ሙሌም የጓደኛውን ሚስጥር ለመጠበቅ የማይፈነቅለው ድንጋይና የማይገባበት ግብግብ አልነበረም። ሙሌ ታማኝነትን፣ ለሚወዱት የሚከፈልን ዋጋ እና የሕሊና ትግል የሚያንጸባርቅ ጠንካራ ማሳያ ነው።

የአቦል ቲቪ ወንድ ገጸ-ባህሪያት፣ በጥንካሬያቸው እና የሰውን ልጅ ስሜት በሚያንፀባርቀው ውስብስብ ማንነታቸው ልዩ ናቸው።

በድጋሚ መልካም ዓለም አቀፍ የወንዶች ቀን!

በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6 እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ tinyurl.com/bdh2j9ed