የዕፀህይወት ድራማ ትኩረት ሳቢ የገፀ ባህሪ ሁሉ የፊት የሚባለው በተንኮል ደረጃም የላቀው በሁለት መለያ የሚጫወተው አሸናፊ በዚህ ድራማ ውስጥ እልም ያለ ቀጣፊ ማስመሰል የተዋጣለት ሁሉም ቦታ ላይ አለው በሚል ወዳጅ መስሎ ጠላት የባህሪ እስስት ነው ።
አሸናፊ በማስመሰል የተዋጣለት ነው ሁሉንም ሃሳብ በማስመሰል ነው የሚያልፈው ከፅህይወት ጋር ያለው ግንኙነት ጭምር በእስስት ባህሪው ወዳጅ መስሎ መቅረቡ ዕፀህይወትን ዋጋ በማስከፈል እረገድ ሚናው ትልቅ ነው ይህ ገፀባህርይ ለጥቅሙ ሲል የማያደርገው የለም ፍላጎት ከነብስ የሚበልጥበት የባህሪ ልዩነት ግድ የማይለው አስመሳይ ባህሪ ያለው ነው ።
አሸናፊ ከነሰብለ ጋር በማበር ጭምር የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ አይኑን በማጉረጥረጥ ፍላጎቱ ለማሟላት ሲል ብቻ ከሁሉም ሰው ጋር ሃሳብ ሳይኖረው ነገሮችን በእሽታ ብቻ በመቀበል ታሪክ አልባ የሰው አገልጋይ ፍላጎት ፈፃሚ የሆነ ነው አሸናፊ በዚህ ልብ አንጠልጣይ ድራማ ውስጥ የሱ ድርሻ የድራማው የታሪክ ፍሰት ላይ ግጭት በመፍጠር ሁነት አስቀጣይ ሆኗል ።
ስምን መልአክት ያወጣዋል ይል የሀገሬ ብሂል ለአሸናፊ የሚሰራ አይደለም ይህ ገፀባህርይ ማሸነፍ ለሱ ገንዘብ ማግኘት ፣ የሰው ሃሳብ ማስፈፀም እዛም እዚም ነው እና በብልህነት የተጓዘ ይመስለዋል ግን ውጤቱ ሌላ ሆኗል ።
በዚህ ማስመሰል ውስጥ የሚዘልቅ ይሆን ግዜ ደጉ መልስ አለው።
አሸናፊ ግን ከራሱ ጋር ማውራት ሲጀምር ወደ ራሱ መመለስ ሲጀምር ምን መልሰ ይኖረው ይሆን ።
አሸናፊ ተፈጥሮን መሆን አልችልም ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀብሎ፣ ሳይደባብቁና ሌላውን ሰው ለመሆን ሳይሞክሩ በነጻነት መኖር ማለት ነው ግን አሸናፊ መሆን ተሳነው ።
ራስን የመሆን ጉልበት የሚመነጨው ማንነትን በመቀበል ነው በራስ መርካት ጭምር የሚመጣው በዚህ ልክ ነው ።
አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ስለማይቀበሉ ራሳቸውን ሆነው መኖር አይችሉም ራሱን መቀበል ያስቸገረው ሰው ላይ የሚታየው የመጀመሪያው ምልክት ራስን አለመሆን ነው፤ የማይቀበሉትን ማንነታቸውን ለውጠው ለመታየት ሲሞክሩ ራሳቸውን ያገኙታል አሸናፊ በዚህ ልክ የመገለፅ ባለ ባህሪ ነው ።
በማንነት ላይ የማልቀበለውን ነገር ለማሻሻል ጤናማ መንገዶችን መሞከሩ ክፋት አይኖረውም፤ ከተሳካልኝ፡፡ ቁም ነገሩ፣ አሻሻልኩትም አላሻሻልኩት ራሴን ወደ መቀበል መምጣቴና ጤናማ የሕብረተሰቡ አካል ሆኜ መኖር አልፈልግም ያለው አሸናፊ በብዙ የባህሪ ውዝግብ ውሰጥ ቀጥሏል ።
አሸናፊ በዕፀህይወት ድራማ ውስጥ የባህሪ መገለጫው ማስመሰል ሆኖ ይዘልቃል ድራማው መልስ አለው ።
