ለወራት ስናስበው እና ስንጠብቀው የቆየነው የ"ግርድ" ድራማ ምዕራፍ ሁለት መምጣቱን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው። ነገር ግን ወደ አዲሱ ምዕራፍ ከመግባታችን በፊት፣ ታሪኩ በየትኛው የልብ አንጠልጣይ ጫፍ ላይ እንደቆመ እናስታውስ።
የአቤል የብቸኝነት እና የብስጭት ትግል
ሆስፒታል ውስጥ አቤል በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነበር። የራሱን ቁስል ለማከም እንኳን ፈቃደኛ ያልሆነው አቤል፣ የአእምሮው ሰላም ተሰርቆ ነበር። የዮሴፍን ምስል እና መኪና በውስጡ እየተመላለሱ፣ እውነትን ፍለጋ ወደ ዮሴፍ በመሄድ በአካልም በአእምሮም ሊሰብረው ሞክሯል። ለዘሪሁን የሰጠው ማስጠንቀቂያ ግን የሁኔታውን አሳሳቢነት ያሳያል፤ ጽዮን ካልዳነች ጭንቅላቱን እንደሚያፈፈነዳው የተናገረው ቃል፣ የቁጣውን ጥግ የሚያሳይ ነበር።
የጽዮን ህይወት እና የእርዳታ እጆች
ጽዮን የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልጋት ሲሰማ፣ አቤል የራሱን ኩላሊት ለመለገስ ፈቃደኛ ሆኖ ምርመራ ጀመረ። ነገር ግን አቤል ለጽዮን ኩላሊቱን መስጠት እንደማይችል ሲረጋገጥ፣ ተስፋ መቁረጥ ተሰሞቶት ነበር። በዚህ መሃል ግን ያልታሰበው ነገር ተከሰተ። የያሬድ ውሳኔ ነገሮችን ለወጠ፤ ያሬድ ያለ ምንም ማመንታት ለጽዮን ኩላሊቱን ለመለገስ ወሰነ።
ከስውር ሴራዎች በስተጀርባ
በሌላ በኩል ታሪኩ አዳዲስ የጥርጣሬ ማዕበሎችን አስነስቷል። የፖሊስ አዛዡ ከዘሪሁን እኩይ ተግባራት ለመላቀቅ ቆርጦ ተነስቷል፤ ሳባን ብቃት ወዳለው መርማሪ ለማምራት ቃል ገብቷል። መርማሪ መክብብ የአቤል እና የጽዮንን የግድያ ሙከራ ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ ነው።
የምዕራፍ አንድ ሲጠናቀቅ ቤቲ እና ዮሴፍ ሲነጋገሩ ማየታችን፣ የሴራው ማዝ እየጠለቀ መምጣቱን ጠቋሚ ነው።
ምን ይጠብቀን ይሆን?
ያሬድ በጽዮን ህይወት ላይ ምን አይነት ተጽእኖ ይኖረዋል? የፍቃዱ ጥርጣሬ ወደ ምን ይወስደናል? ቤቲ እና ዮሴፍ በጋራ እያሴሩ ያሉት ሴራ ምን ይሆን?
የ"ግርድ" ምዕራፍ ሁለት ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እና እጅግ አጓጊ የሆኑ አዳዲስ ምስጢሮችን ለመግለጥ ዝግጁ ነው።
"ግርድ" ምዕራፍ ሁለት ማክሰኞ ሰኔ 30፣ ከምሽቱ 2፡00 በ አቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል፣ እንዳያመልጥዎ
የአቦል ድራማዎች እንዳያመልጥዎ ደምበኝነትዎን ያስቀጥሉ፡ https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa
