Logo

እስካሁን በአፋፍ ቴሌኖቬላ ያስገረሙን ስድስት ክስተቶች!

ዜና
01 ኦገስት 2023
አፋፍ ቴሌኖቬላ በሳምንት አምስት ቀን አጓጊ ታሪክ ያቀርብልናል፣ ከእነዚህ ታሪኮች በጣም ያስገረሙን እነዚህ ነበሩ።
shocking moments on afaf article

የዙማ መንደር ኗሪዎች ህይወትን የቀየረው አንድ ድርጊት ነው። በአፋፍ ተራራ ላይ የተደበቀውን ኦፓል ለማግኘት ምንም ከማድረግ ወደኋላ የማትለው እስከዳር፣ የዋሴን ህይወት እሱ ብቻ ከሚያውቀው እውነት ጋር ቀጭተዋለች። ይህ ድርጊት ባላሰበችው መንገድ የመንደሩን ኗሪዎች ህይወት ቀይሯል።

በዚህ ምክንያት የተከሰቱት ስድስት አስገራሚ ጊዜያቶች እነዚህ ናቸው፡

  1. ፍርቱና የእስከዳርን ወንጀል ለመደበቅ ካሳ ትፈልጋለች።

ፍርቱና፣ የዋሴ ገዳይ እስከዳር መሆኗን በአጋጣሚ ትደርስበታለች። ይሄንን ምስጢር ለመጠበቅ ግን ከእስከዳር ለእናቷ ቤት፣ ለእራሷ ስራ እና የመስራቤት ድርሻ ትፈልጋለች። በተጨማሪም እስከዳር ከቤቷ እና ልጇ ስታገላት በመቆየቷ ቂሟን መወጣት ትፈልግ ነበር። ነገር ግን ፍርቱና እቅዷን ሳታሳካ እስከዳር በማገት እና ቤቷን በማቃጠል ልትገላት ትሞክራለች።

  1. የእንቆጳ ወላጆች ማንነት ይጋለጣል።

እንቆጳን ያሳደጓት ዋሴ እና ሽቱ ናቸው ነገር ግን የወለዷት ወላጆቿ ማንነት ያልተጠበቀ ነው። የዋሴ የድሮ ጓደኛ አብዮት እና እስከዳር የእንቆጳ ወላጆች እንደሆኑ እና ይሄን ሳያውቅ ከአፋፍ አንስቶ ያሳደጋት ዋሴ መሆኑ ተጋልጧል።

  1. እስከዳር የፍርቱናን ቤት አቃጥላ ፈንጂ ትልክላታለች።

ፍርቱና ከእስከዳር ካሳ ለማግኘት ያደረገችው ጥረት አደጋ ውስጥ ብቻ እንደከተታት ስትረዳ የእስከዳርን ምስጢር ለመጠበቅ 10 ሚሊየን ብር ትጠይቃለች። በዚህ ጊዜ ይሳካላታል ብላ ያሰበችው እቅድ፣ ፈንጂ በመሆኑ የሁላት ሰውን ህይወት ይቀጫል።

  1. ፍርቱና እውነቱን ለፖሊስ ታጋልጣለች።

ፍርቱና የእቅዶቿን መበላሸት ስትረዳ እውነቱን ለፖሊስ ለማጋለጥ ትወስናለች። ነገር ግን ኢንስፔክተር ደጀኔ እውነቱን ሸሽጎ ከእስከዳር ብር በመቀበል ሙስና ይሰራል። እውነቱን አጋልጣ ነፃ መሆን የተመኘችው ፍርቱና ሌላ እስርቤት ውስጥ ትገባለች።

  1. እንቆጳ የአባቷን ገዳይ ማንነት ታውቃለች።

በእስር እና በእስከዳር ግድያ ሙከራዎች የተማረረችው ፍርቱና ከታሰረችበት አምልጣ እንቆጳን ለማግኘት ትሞክራለች። ነገር ግን በቅርብ እየተከታተላት የነበረው ታምራት በመጨረሻው ደቂቃ በጥይት ይመታታል። በእሳት፣ ፈንጂ እና ጥይት የደከመችውን ፍርቱና ከማገቱ በፊት ግን ለእንቆጳ የአባቷን ገዳይ ማንነት ታጋልጣለች።

  1. እንቆጳ ለእስከዳር መስራት ትጀምራለች።

እንቆጳ ፍርቱና ያጋለጠችውን ትልቅ ሚስጥር ይዛ ለፖሊስ አለማቅረቧ ሲያስገርመን እስከዳርን ለስራ ትጠይቃታለች። እንቆጳ የአባቷ ገዳይ ጋር መስራት የጀመረችው በእስከዳርን በቅርብ በማጥናት መረጃ ለማግኘት እንደሆነ እንረዳለን።

ይህ አስፈሪ እቅድ ለእንቆጳ ይሳካላት ይሆን? ወይስ እንደ ፍርቱና ህይወቷን አደጋ ውስጥ ይጥለዋል?

ይሄን ለማወቅ አፋፍን ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉ!