Logo
AbolTV Yebasilikos enba S1 SLIM BILLBOARD
channel logo

Yebasilikos Eniba

465DramaPG13

ብርሀን ሲያስጨንቋት ለኖሩት ጥያቄዎች መልስ ትፈልጋለች - የባስሊቆስ ዕንባ

ዜና
30 ኖቬምበር 2023
ብርሀን እስካሁን ስለ ቤተሰቧ ምስጢር ያገኘቻቸው መልሶች ይበልጥ ግራ የሚያጋቡ ጥያቄዎችን ፈጥረውሏታል።
birhan - yebasilikos enba

የባስሊቆስ ዕንባ ብርሀን የተባለች የአንዲት ወጣትን ውስብስብ የቤተሰብ ታሪክ ያስቃኛል። ብርሀን እስካሁን ባየናቸው ክፍሎች ውስጥ ስለ ቤተሰቧ አንድ አንድ መልስ ደርሳባቸዋለች። እነዚህ መልሶች ግን ይበልጥ ግራ የሚያጋቡ ጥያቄዎችን ፈጥረውሏታል። ጥያቄዎቿ እና እስካሁን ያገኘቻቸው መልሶች እነዚህ ናቸው፡

የእናቷ ጅብ መሆን

ብርሀን እናቷን ደግማ ላለማየት ወስና አዲስ አበባ ከሄደች በኋላ፣ የቤተሰቧ ስም እየጠፋ መሆኑን ስትሰማ ወደ ዳባት ተመልሳለች። ዳባት ስትደርስም ህብረተሰቡ እናቷ ጅብ ነች ብለው እንደሚያምኑ እና ቤተሰቧን እያገለሉ መሆኑን ትረዳለች። ይሄን ወሬ ለማጥፋት እናቷን አንድ ማታ ስትከታተላት፣ እናቷ ከድሮ ፍቅረኛዋ አበራ ጋር እየተገናኘች መሆኑን እና የታናሽ ወንድሟ አቢ አባት መሆኑን ትረዳለች። እራሱን እብድ አስመስሎ በሰፈራቸው ሲኖር የቆየው ሰው አበራ መሆኑን እናም እናቷ በድብቅ እያገኘችው እንደምትኖር ትደርስበታለች። ስለዚህም ያላት ጥያቄ፣ ከአበራ ጋር ፍቅሯን የምትቀጥል ከሆነ ለምን እናቷ ወደ ህይወታቸው ተመልሳ መጣች የሚለው ነው።

የአበራ ማንነት

ብርሀን፣ አበራ የተባለውን ስም ከእናቷ የሰማችው በልጅነቷ ቤት ውስጥ ተደብቃ እያለች ነበር። ከዛ ጊዜ በኋላ የአበራ ማንነት እና ከእናቷ ጋር ስላለው ግንኙነት ጥያቄ አድሮባታል። ባለፈው የየባስሊቆስ ዕንባ ክፍል እንደተረዳነው ከሆነ የአበራ ማንነት ከእናቷ መጥፋት ጋር የተያያዘ ነው። በተጨማሪም በአስገራሚ ሁኔታ፣ አበራ የእናቷ የድሮ ፍቅረኛ መሆኑን ትደርስበታለች። ይሄን ምስጢር ለማንም ሳትናገር በጭንቀት ውስጥ የቆየችው ብርሀን፣ ከፍቅረኛዋ ሙሌ ጋር ምስጢር እንድትደብቅ ትገደዳለች።

Abol TV Yebasilikos enba S1 Poll Background
yebasilikos enba poll 3

ፍቅረኛዎ የቤተሰብዎን ምስጢር መንገር አለበት ብለው ያምናሉ?

አዎ0%
አይ ሁሉም መታወቅ የለበትም0%

የአበራ “ሞት”

ይህ ሁሉ ምስጢር ከተጋለጠ በኋላ በአስገራሚ መንገድ አበራ እንደሞተ እንሰማለን። ነገር ግን አበራ ብርሀንን የባስሊቆስ ወንዝ ሊያገኛት ሄዶ አለመሞቱን ያጋልጣል። አበራ ለብርሀን የራሱን ሞት ለምን እንዳስመሰለ ሊነግራት ይሞክራል ግን መስማት አትፈልግም። ነገር ግን ብርሀን የእናቷን የፍቅር ህይወት ለማገናዘብ ስትሞክር የእራሷ ፍቅር ግንኙነት ላይ ችግር ይፈጠራል። አበራን ለመስማት ፍቃደኛ የምትሆን ይመስልዎትላ?

Abol TV Yebasilikos enba S1 Poll Background
yebasilikos enba poll 4

እርስዎ በብርሀን ቦታ ቢሆኑ እናትዎን ይቅር ይላሉ?

አዎ0%
አይ0%

ብርሀን እራሷን ስትጠይቅ የቆየችው ጥያቄ በነገው ማታ የባስሊቆስ ዕንባ ክፍል መልስ ያገኛል። የባስሊቆስ ዕንባ አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ዱካ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 እንዳያመልጥዎ!