Logo
Gizze S1
channel logo

Gizze

465TelenovelaPG13

ጊዜውን የሚመጥነው የአቦል ቴሌቪዥን አዲሱ ተከታታይ ቴሌኖቬላ “ጊዜ”

ዜና
05 ጁን 2023
ጋዜጣዊ መግለጫ
gizze press release

አዲስ አበባ፡   ተወዳጅና ጊዜውን የሚመጥኑ ይዘቶችን ለተመልካቾች እያቀረበ የሚገኘው አቦል ቴሌቪዥን አሁንም ማራኪ የሀገር ውስጥ ተከታታይ ቴሌኖቬላዎቸችን ማቅረቡን ቀጥሏል። ከሰኞ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ጊዜ የተሰኘ ድንቅ ቴሌኖቬላ ለእይታ ያበቃል፡፡

አዲሱ ተከታታይ ቴሌኖቬላ ጊዜ በአንድ ወቅት እጅግ የተከበረ ባለሀብት የነበረና ባልሰራው ወንጀል 20 ዓመታትን በእስር ያሳለፈውን ገጸባሕሪይ “ጀምበሩ”ን ታሪክ ይተርክልናል።

በጊዜ ቴሌኖቬላ ከእስር የተፈታው ጀምበሩ ስሙን ለማደስ እና ህይወቱን ለመመለስ ረጅምና ፈታኝ ትንቅንቅ ይገጥመዋል። ይህ ውጣውረድ እስከመጨረሻው በአጓጊ የታሪክ አወቃቀር፣ በድንቅ ትወና እና በፕሮዳክሽን ጥራት ታግዞ ይዘልቃል

በአንተነህ ኃይሌ ፕሮዲዩስ በተደረገው በጊዜ ቴሌኖቬላ ከተስፋዬ ሲማ በተጨማሪ ስመጥሮቹ አርቲስቶች አለባቸው መኮንን፣ ሄኖክ በሪሁን፣ ትነበብ ተረፈና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡

ቴሌኖቬላው በፍቅር እና በህይወት ሽክርክሪቶች ታጅቦ የሚዘልቅ መሆኑ ተመልካቾችን እስከ መጨረሻው ግምታቸውን ያንረዋል፡፡

የአቦል ቻናል ማናጀር ሰርካዲስ መጋቢያው፡ "አቦል ቲቪ መረጃ ሰጪ፣ አዝናኝ እና አነቃቂ ይዘትን ለመፍጠርና ለተመልካቾች ለማቅረብ ባለው ቁርጠኝነት” በትጋት መቀጠሉን ገልጻ “ጊዜ ለተመልካቾች የማይረሳ የሃገር ውስጥ ቴሌኖቬላ እንደሚሆን እምነት አለኝ” ብላለች፡፡ አክላም “ይህንን አስደናቂ ቴሌኖቬላ ለተመልካቾቻችን ለማድረስ ጓጉተናል”ብላለች፡፡

ተመልካቾች ይህንን ድራማ በአቦል ቴሌቪዥን ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ምሽት 2፡30 ጀምሮ መከታተል ይችላሉ፡፡