Logo

በግንቦት ወር በአቦል ቲቪ እነዚህን ዝግጅቶች ይመልከቱ!

ዜና
12 ሜይ 2023
እነዚህን የአቦል ቲቪ አቅርቦቶች በመመልከት ግንቦትን በሳቅ እና ጨዋታ ያሳልፉ።
watch this May abol article

የክረምት ወቅት በሚቃረብበት ጊዜ መዝናኛችን በቤታችን እንመርጣለን። አክሽን፣ ፍቅር፣ ውድድር እና ኮሜዲን የሚያካትቱ፣ ለሁሉም ዝግጅቶች የሚመጥን አቀራረብ በአቦል ቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ቀደመው ያጣጥሙ።

እነዚህን ዝግጅቶች መከታተል ይችላሉ!

እንደ አንድ ምዕራፍ 1 | ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 200

በእንደ አንድ ነገሮች እየተወሳሰቡ ነው! ፍቅርተ ከገባችበት አጣብቂኝ ሁኔታ ለመውጣት እየሞከረች ነው። ነገር ግን መንገዱ እየጠበበባት መጥቷል። ከገባችበት አጣብቂኝ መውጣት ትችል ይሆን?

ደራሽ ምዕራፍ 1 | ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30

በመላኩ እና ልዑል ላይ በደረሰው የመኪና አደጋ ምክንያት ብሌን ስለ ግንኙነታቸው ደብቃው የነበረው እውነት ተጋልጧል። በዚህም መሀል ኢንስፔክተር አማረ የመብራቱን መጥፋት እና የጌታቸውን ግድያ እየመረመረ ነው፣ ምስጋና ለማምለጥ እየሞከረው ያለው እውነት ይጋለጥ ይሆን?

አጋፋሪ ምዕራፍ 2 | ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 300

የአጋፋሪ እና ጥንቅሹ ጥምረት፤ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ የሚያርፉት አስክሬኖች ከአጋፋሪ ጋር በመንፈስ በመወያየት ልዩ ልዩ የህይወት ታሪኮችን ያጋሩናል። ይሄንንም ጥንቅሹ ግራ እንደተጋባ ይመለከታል። ይበልጥ አስደናቂ ታሪኮችን በአጋፋሪ ይከታተሉ።

ሳሎኑ ምዕራፍ 1 | ዘወትር እሮብ ከምሽቱ 2:30

በመላው አለም የውበት ሳሎን እና የሰፈር ታሪኮች እጅ ለጅ ነው የሚሄዱት። የኤልሳ ሳሎንም ይሄን ደንብ ተከትሎ ከጸጉር ማስተካከል አልፎ ማህበራዊ ጉዳዮችን እያዝናና እና እያሳሳቀ ያቀርብልናል።

ስውር ምዕራፍ 1 | ዘወትር እሮብ ከምሽቱ 300

ግሩም ለዳናዊት የሚሰማውን የድሮ ስሜት በንዴት ሸፍኖ እውነቱን መጋፈጥ አይፈልግም። ዳናዊት በተቃራኒው የድሮ ፍቅራቸውን እያስታወሰች በትዳሯ መደሰት ያቅታታል። የግሩም እና ዳናዊት መጨረሻ ምን ይሆን?

አቦል ሚሊየነር ምዕራፍ 1 | ዘወትር አርብ ከምሽቱ 1:30

አቦል ሚሊየነር በምዕራፍ 2 አንደኛ እና ሁለተኛ የሚወጡ ተወዳዳሪዎችን ተሸላሚ ለማድረግ ውድድሩን ጀምሯል። የአንድ ሚሊየን ብር ተሸላሚ ለመሆን የጠቅላላ እውቀት ተፈትኖ ማለፍ ያስፈልጋል፣ የዚህ ዙር አሸናፊ ማን ይሆን?

ምስኪኖቹ ምዕራፍ 2 | ግንቦት 14 ክምሽቱ 1:30 ይጀምራል

በአማት እና ምራት መሀል የሚፈጠሩት አለመግባባቶች በአስቂኝ መንገድ በምስኪኖቹ ድራማ ይቀርባል። እዩ፣ በእናቱ እና ሚስቱ መሀል የሚከሰቱትን አለመግባባቶች በሰላም ለመፍታት ሙከራውን ይቀጥላል። በምዕራፍ 2 በኤደን እና ሙልዬ መሀል የተፈጠሩትን ልዩ ክስተቶች በምስኪኖቹ ይከታተሉ!