Logo

በሐምሌ ወር ላይ እነዚህን ታሪኮች በአቦል ዱካ ይመልከቱ!

ዜና
11 ጁላይ 2023
ብርድ እና ዝናብ ቤታችን በሚያስቆየን ጊዜ እነዚህ ድራማዎች ያዝናኑናል።
july article duka

በአቦል ዱካ ሁሉም አለ። ኮሜዲ፣ ሪያሊቲ ሾው እና ድራማ የመረጡትን ይመልከቱ!

በአደይ ላይ፣ ወ/ሮ ሮማን ስለቤተሰባቸው ያወቁት አዲስ እውነት እራስ ምታት ሆኖባቸዋል። ነገር ግን የራሄልን ጭንቀት የተገነዘበችው አለላ፣ ወ/ሮ ሮማን ጭንቀታቸውን እንዲረሱ ታዝናናቸዋለች። ይሄን ያልተጠበቀ ጓደኝነት ዘወትር ከሰኞ -አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይከታተሉ።

በጎጇችን ላይ፣ ሙሽሮች የሰርጋቸውን ቀን እራሳቸው እና ቤተሰቦቻቸው ደስተኛ ለማድረግ ዝግጅታቸውን ይቀጥላሉ። በጎጇችን ላይ የአንድ ጥንድ ሰርግ ከእቅዱ እስከ ሰርግ ቀን ባለው ጊዜ የሚያደርጉትን ዝግጅት እና የሰርጋቸውን ቀን ዘወትር አርብ ከምሽቱ 1፡00 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ 466 ይከታተሉ።

በጥላ ላይ፣ የጫካ ምስጢር ሊጋለጥ ነው። ዘወትር ፍኖትን አግቶ ባለበት ጊዜ ላይ የጫካ ትልቅ ሚስጥር ይጋለጣል። ፍኖት አባቷን ይቅር ማለት ትችል ይሆን? ታሪኩን ዘወትር አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይከታተሉ።

በናፍቆት ላይ፣ ግሩም ለምርመራ ፖሊስ ጣብያ ገብቷል። ነገር ግን የደጀኔ እና ሰውነት አለመግባባት ምርመራውን እያደናቀፈ ነው። የግሩም እና ቃልአብን ግንኙነት የሚደርሱበት ከሆነ ናፍቆትን ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 በመከታተል ይወቁ!

እነዚህን አጓጊ የአቦል ዱካ ዝግጅቶች ያጣጥሙ! አቦል ዱካ በዲኤስቲቪ ቻናል 466 ብቻ ያግኙት!