Logo

ፍትህን ፍለጋ – የተገፉት

ዜና
13 ጃንዩወሪ 2022
የሊንዳ ከባድ ጉዞ።

የሊንዳ ህይወት አቅጣጫውን የቀየረው እናቷ ሩሃማ በፌኔት ግድያ ስትከሰስ ነው። ጠበቃ ለመሆን ለስራ ቃለ-መጠይቅ ከቀረበች በኋላ እናቷ ባልፈጸመችው ወንጀል መከሰሷን ትረዳለች።

በልጅነቷ አባቷን በተሳሳተ ክስ ምክነያት አጥታ ስለነበር  ፖሊሶች የሩሃማን ንፅህና መገንዘብ እንደማይፈልጉ ስትረዳ እውነቱን ለማጋለጥ ትወስናለች። የፌኔት ገዳይ በቅናት የተሞላችው ላምሮት መሆኗን ደርሳበት መረጃውን ለመስረቅ ትሞክራለች። መረጃው ግን ግድያውን በመሰከረችው የቤት ሰራተኛ ውብዬ ይወሰዳል። ላምሮት መረጃና ምስክር መኖሩን ስትረዳ ባልለቤቷ ጴጥሮስ ውብዬን እንዲግድላት ታደርገዋለች።

ጴጥሮስ በመጀመሪያ ሚስቱ ፌኔት ሞት ምክነያት ሀዘን ላይ በመሆኑ ውብዬን እንድታመልጥ ይረዳታል። የእናቷን ንፅህና የሚያጋልጠው መረጃ ከውብዬ ጋር ሲጠፋ ሊንዳ ምርጫ ከማጣቷ የተነሳ እራሷን የቤት ሰራተኛ በማስመሰል የጴጥሮስ እና ላምሮት ቤት ለመሰለል ትገባለች። በዚህ ጊዜ ፌኔት በኑዛዜ ንብረቷን ሁሉ ለሩሃማ መስጠቷን ላምሮት እና ጴጥሮስ ይደርሱበታል። ላምሮትም ውርሱን ለማስቆም እስርቤት ውስጥ ሩሃማን ታስገድታለች። ላምሮት እና ጴጥሮስ ያሸነፉ በመሰላቸው ጊዜ ላይ ንብረቱ ለሩሃማ ልጆች እንደሚዘዋወር ይሰማሉ። ልጆቹን ለማግኘት ሲሞክሩ የሊንዳ ፍቅረኛ ማኪ ለመደበቅ ይረዳታል እናም እቅዷን እንድታሳካ ታናሽ ወንድሟ ቶማስን ይንከባከበዋል።

ሊንዳ በነላምሮት ቤት ውስጥ መረጃ ለማግኘት ትሞክራለች። ጎረቤት የምትሰራው የውብዬ እህት ማርዬ ስለውብዬ መሰወር በመጨነቋ ለመፈልግ ትሞክራለች እናም ሊንዳ የእህቷን ስራ ነጥቃለች ብላ በማሰቧ ትጠላታለች። ግን በሩሃማ ለቅሶ ላይ የሊንዳን ማንነት ስትደርስበት ሊንዳ ውብዬን ለምን እንደምትፈልጋት ታስረዳታለች። በመጨረሻ ሊንዳ ውብዬን ስታገኛት ውብዬ መረጃውን ለመስጠት ትስማማለች ግን ቃልዋን አጥፋ ጴጥሮስን ስለሊንዳ ለማስጠንቀቅ ስትሞክር ላምሮት ትገድላታለች። ሊንዳም ከማርዬ እርዳታ ጋር ስታፈላልገው የነበረው መራጃ ከውብዬ ጋር ይጠፋል። ላምሮት ሊንዳን መጠርጠር በመጀመሯ የሊንዳን ክፍል ስትፈትሽ ስለ ማንነቷ ታውቃለች።

ጴጥሮስ እና ላምሮት የፌኔትን ሃብት ለማግኘት ብለው ሊንዳን ለመግደል ሲሞክሩ ማኪ በስህተት ይሞታል። ሊንዳ የምትወዳቸው ሰዎች አንድ በአንድ ሲሞቱ ፍትህ ለማግኘት የነበራት ተስፋ አብሯቸው ይሞታል። ላምሮት እና ጴጥሮስ ማርዬን ቀጥረው የራት ዝግጅት በሚያደርጉበት ቀን ሊንዳ ለበቀል ትመጣለች። ብቻዋን በመሆኗ ግን ባልና ሚስቱ ያግቷታል እና የፌኔት ሃብት እንዳትቀበል እንድትስማማ ያሰቃዩአታል። ከታገተችበት አምልጣ ልትገላቸው ትሞክራለች እናም በዚ ማሀል የምታገኛት ማርዬ ትረዳታለች።

ሊንዳ የእናቷ እና ፍቅረኛዋን ገዳዮች ትበቅላለች ግን ለዚህም ትልቅ ዋጋ ትከፍላለች። ስለሊንዳ ምርጫ ምን ያስባሉ? ፖሊሶች ይይዟት ይሆን?

የተገፉት ምዕራፍ 1 ተጠናቋል፣ ምዕራፍ 2 ሲጀምር እናሳውቆታለን።