Logo

ዮቶራውያን - ከድማው ምን እንጠብቃለን?

ዜና
29 ዲሴምበር 2021
ስለአዲሱ የአቦል ቲቪ አቅርቦት ዮቶራዉያን።

ሰስፔንስ፣ የሀገር ታሪክ እና አክሽን ያለው ድራማ ይወዳሉ? መልስዎ አዎ ከሆነ ስለዮቶራዉያን የተሰኘው አዲሱ የአቦል ቲቪ አቅርቦት ለማወቅ ማንበብ ይቀጥሉ!

1640773944 27 screenshot 2021 12 29 at 11.08.54

አብራሃም የ12 አመት ልጅ እያለ አባቱ ከስራው ጋር በተያያዘ አደጋ ምክነያት ተሰውሯል። ከዛ ጊዜ በኋላ በተደጋጋሚ በህልሙ ለሀገርህ እና ህዝብ ታስፈልጋለህ የሚል ድምጽ ይሰማል። ህልሙ አባቱ የሚያጠናው የነበረው የሀገር ቅርጽ እና የተሰወረበት ምክነያት ጋር የተያያዘ ነው።

1640774293 27 screenshot 2021 12 29 at 11.15.56

አብረሃም በህልሙ የሰማው ድምጽ ባለቤት ማንነት ይደርስበት ይሆን? የአባቱን ምርምር በማጥናት የተሰወረበትን ምክነያት ሊደርስበት ይሞክራል። ቅርጹን በእጃቸው ለማስገባት ከሚፈልጉ ሰዎች ቀድሞ ይደርስበት ይሆን? ይሄን ለማወቅ ድራማውን በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!

ዮቶራዉያን ታህሣሥ 21 በአቦል ቲቪ ይጀምራል!