Logo
Ende And S1
channel logo

Ende And

466TelenovelaPG13

ከፍቅርተ ፍጹም ሕይወት በስተጀርባ ምን ተደብቋል? – እንደ አንድ

ዜና
11 ማርች 2024
ፍቅርተ በህይወቷ ሁሉም ነገር የተሟላላት ትመስላለች። ነገር ግን የደበቀችው ነገር እንዳለ ግልጽ ነው። ምን ልትደብቅ ትችላለች?
ende and - the perfect life article

እንደ አንድ በአቦል ዱካ በቅርብ ቀን የጀመረው የቤተሰብ ድራማ ሲሆን፣ ከመጀመሪያው ክፍል ጀምሮ በተለያዩ ዘውጐች ትኩረታችንን ስቦታል ነው። ፍቅር፣ ቤተሰብ እና ምስጢራዊነት ያለው ድራማ ነው ነገር ግን እኛ ይበልጥ ማወቅ የምንፈልገው የዋና ገጸ-ባህሪዋ የፍቅርተን ሕይወት ነው።

ከውጭ ሲታይ ፍቅርተ ሁሉንም ነገር ያላት ይመስላል –  ጥሩ ልጆች፣ ጥሩ ባል፣ ጥሩ ሥራ እና ፍጹም ሕይወት። ውድ ተመልካቾቻችን በፍቅርተ ሕይወት ውስጥ ሁሉም ነገር እንደምናየው አይደለም፣ ምክንያቱም አንድ ጥላ ከመጀመሪያው ክፍል ጀምሮ ይከተላታል። የተበሳጨው ሥራ አስኪያጅዋ ፍቅርተ በሥራዋ ላይ ችግር እንደፈጠረች አሳውቋታል። በሥራ ላይ መተኛት? ይህ ፍጹም ህይወት ላለው ሰው የማይታመን ስራ ይመስላል።

ከዚህም ባሻገር ዋነኛዋ ገጸ ባህሪያችን በቤት ውስጥ በሥራ ተጠምዳ ለልጆቿ፣ ለሳም፣ ለአቤል እና ለማትዩ ፍጹም እናት እና ለባሏ ለበረከት ፍጹም ሚስት ሆና ትገኛለች። ነገር ግን ይሄን ስራ ብቻ አይደለም የያዘችው! ፍቅርተ ባለቤቷ በሥራው ደስተኛ አለመሆኑን አስተውላለች እናም እሱን ደስተኛ ለማድረግ ቆርጣ ተነስታለች፣ ስለዚህ ምን ታደርጋለች? ፒያኖ ትገዛለታለች እና ወንድሟ እሱ እንደገዛው እንዲናገር ትጠይቃለች። ነገር ግን ለራሷም ቢሆን በሥራዋ ላይ ችግር እያጋጠማት ነው ስለዚህ ለፒያኖ የሚሆን ገንዘብ ከየት አገኘች?

ውድ ተመልካቾቻችን እናንተ የምትጠይቋቸውን ተመሳሳይ ጥያቄዎች እየጠየቅን ነው። ሌላ ደግሞ ቤተሰቦቿ ምግብ ለመብላት ሳህኖቻቸውን እንዲለዋወጡ አለመፍቀዷ በጣም አጠራጣሪ ነው። ሁሉም አንድ ዓይነት ምግብ እየበሉ  ስለሆነ ከየትኛውም ሳህን ቢበሉ ምን ለውጥ ያመጣል? ይህ ሁሉ ግራ የሚያጋባ ባህሪ በጠረጴዛዋ ላይ ቁጭ ብላ በዜና ላይ ከነበረው ምስጢራዊ ቡድን ጋር የተያያዘ ካርድ ይዛ ስናያት የበልጡ ጥያቄዎችን ያመጣብናል። ስለዚህ እኛ መጠየቅ አለብን፣ ፍቅርተ ምንድን ነው የደበቀችው?

የዚህን አስገራሚ ድራማ ቀጣይ ክፍሎች ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡30 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይመልከቱ። በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed