Logo
Abol Duka Zuret S1 Slim Billboard Desktop

ሰለዙረት ተዋናይ ሩታ መንግስተአብ እና ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ) በሽገር ጣቢያ ቆይታ ላይ የተረዳናቸው ነገሮች። - ዙረት

ዜና
16 ሴፕቴምበር 2021
ስለሩታ እና ሳምሶን::

በአዲሱ አመት ዋዜማ ላይ የአቦል ቲቪ ዙረት ድራማ ላይ ምዕራፍ እና ሱራፌል ሆነው የሚተውኑት ሩታ መንግስተአብ እና ሳምሶን ታደሰ ሸገር ሬዲዮ ጣብያ ላይ ቀርበው ነበር። ከሽመልስ በቀለ ጋር ተዋናዮቹ ባደረጉት ቆይታ ላይ ስለህይወታቸው አዳዲስ የተረዳናቸው ነገሮች ነበሩ።

1. የሩታ አዲስአመት

በሚያስቅ ሁኔታ ለበዓል ከቤተሰብ ጋር ካደረገችው ዝግጅት በኋላ በዓሉን ቀን ግን በወረፋ ምክንያት ፀጉር ቤት ብዙ ጊዜ እንዳሳለፈች አጫውታናለች።

2. የቲያትር ስራ ለበዓል አያቆምም

ሳምሶን በዓል ቀን ላይ ቲያትር ቀርቦ ያሳልፋቸውን ቀናት ያስታውሳል። በቅርብ ጊዜ ቅርጫት ኳስ መጫወት እንደጀመረ እና በቲያትር የማያሰልፋቸውን ቀናት ቅርጫት ኳስ በመጫዎት እንደሚያሳልፍ አሳውቆናል።

3. ስለዙረት ገፀ-ባሕሪያቸው ተዋናዮቹ ምን ያስባሉ?

ሩታ የዙረት ገፀ-ባሕሪዋ ምዕራፍ እንደምታሳዝናት እና ወዳት የምትተውናት ገፀ-ባሕሪ እንደሆነች አሳውቃናለች። የሳምሶን ገፀ-ባሕሪ ሱራፌል ልዩ እና ምስጢራዊ ባህሪ ያለው ሲሆን ይሄን ጥልቅ ገፀ-ባሕሪ መጫዎት እንደተመቸው አሳውቆናል።

Zuret Poll Question 3000 x 1200
ዙረት ሸገር FM

የማንን ገጸ ባህሪ በጣም ይወዳሉ?

ሩታ25%
ሱራፌል75%

4. አሳዝኗቸው የተጫወቱት ገፀ-ባሕሪ

ሩታ ከእለታት የተባለው ፊልም ላይ የተጫወተቻት ገፀ-ባሕሪ እንደምታሳዝናት አሳውቃለች። ምርጫው ሰውን ትንሽ ግራ ሊያጋባ ይችላል ብሎ ያሰበው አሳዛኝ ገፀ-ባሕሪ ብቸኛ የነበረው የሻይሎክ የተባለው ገፀ-ባሕሪ ነው።

5. ሳምሶን እና ሩታ “የአራዳ ሰፈር” ቄራ ነው ያደጉት

ቄራ በሚያድጉበት ጊዜ ባይተዋወቁም ሩታ እና ሳምሶን ስለአካባቢው እና ከሰዎች ጋር ትረዳድቶ የመኖሩን መንፈስ እንደሚወዱት ተናግረዋል::

ዙረት ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ 146 ይከታተሉ!

በሸገር ጣብያ የነበራቸውን ቆይታ ለማዳመጥ በዚህ ቪዲዮ ይመልከቱ!