በአቦል ቲቪ አዲስ የጀመረውና የብዙዎችን ቀልብ የገዛው “በምስጢር” ድራማ፣ ከላይ ከሚታየው ፈገግታ ጀርባ ያለውን ጥቁር ምስጢር እየገለጠ ይገኛል። እስካሁን የተመለከትናቸውን ልብ አንጠልጣይ የታሪኩ ክፍሎች እነሆ፦
የተዓምር መከራ፦ ሕልሟን የበላው ድንገተኛ ማዕበል
ሐኪም ሆና ወገኗን ለመርዳት ሌት ተቀን የምትተጋው ተዓምር፣ ለሕይወቷ ስኬት ወሳኝ በሆነው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዋዜማ ላይ ከባድ መርዶ ደረሳት። ብቸኛ መከታዋ የነበሩት እናቷ በድንገት እራሳቸውን ማጥፋታቸው ስትሰማ ተዓምር እራሷን ሳተች።
ከሐዘኗ ገና ሳትጽናና ግን ሌላ መዓት መጣ፤ አንድ እንግዳ ሰው ደጃፏ ላይ ቆሞ እናቷ ለሕክምና ብድር ቤታቸውን በመያዣነት እንዳስያዙና ቤቱን ሊረከብ እንደሚችል ነገራት። በሐዘን ላይ መከራ የተደራረበባት ተዓምር፣ ተስፋዋን ሰንቃ ወደ አዲስ አበባ አክስቷ ዘንድ እርዳታ ለማግኘት የጭንቀት ጉዞዋን ጀምራለች።
የሰለሞን አታላይነት፦ የማህሌት የ12 ዓመት ድካም ወዴት ፈሰሰ?
ለአስራ ሁለት ዓመታት በስደት በአረብ ሃገር ስጸራ የነበረችው ማህሌት፣ “ሙሉጌታ” ብላ ለምታምነው ፍቅረኛዋ ሰለሞን የላከችው ገንዘብ ትልቅ ቤት እንደሚገነባላት ታስብ ነበር። ነገር ግን ሀገር ቤት ስትመለስ ያገኘችው ሀቅ የልብ ስብራት ሆነባት።
ሰለሞን ከሌላ ሴት (ሀዊ) ጋር ትዳር መስርቶ የሚኖር አጭበርባሪ መሆኑን ያወቀችው፣ በቆየችበት ሆቴል ጥሎት በሄደውና የባለቤቱን ስም በያዘው የጋብቻ ቀለበት ነበር። የአስራ ሁለት ዓመት ላቧን የበላውን ይህን ሰው፣ ማህሌት በዝምታ አታልፈውም፤ አሁን ከእህቷ ጋር ሆና የሰለሞንን ዓለም የሚያናጋ የበቀል እሳት እያዘጋጀች ነው።
የሂሩት ስጋት፦ ከአዲስ አበባ የተሸሸገው ምስጢር
በአርባ ምንጭ ከተማ ከቤተሰቧ ጋር በሰላም የምትኖረው ህሩት፣ ባለቤቷ በአዲስ አበባ የሥራ ዕድል ማግኘቱን ሲነግራት ደስታ ሳይሆን ታላቅ ፍርሃት ወረራት። አዲስ አበባ ለሂሩት የምቾት ከተማ ሳይሆን፣ የሸሸችበትና ምስጢሯ የተቀበረባት ስፍራ ናት።
ባለቤቷ የሰለሞንን አጓጊ የሥራ ግብዣ ተቀብሎ ወደ ዋና ከተማው ለመመለስ ሲወስን፣ የሂሩት ዓለም መጨለም ጀመረ። ሂሩት የሸሸችው ምስጢር ምንድነው? አዲስ አበባስ የተቀበረውን እውነት ታወጣው ይሆን?
ምስጢሮች እየተገላለጡ፣ በቀል እየተቀጣጠለ ነው!
ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በ አቦልቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ።
በ #MyDStv መተግበሪያ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6
በ DStv Stream መተግበሪያ የሚወዱትን ድራማዎች ይከታተሉ!
