Logo

የአደይ ፌስቡክ ላይቭ ቻት እንዳያመልጥዎ!

ዜና
15 ጁን 2021
የሰኔ አርብ ምሽቶች በጣም አስደሳች ሊሆኑ ነው።

የአቦል ቲቭን ተወዳጅ ገጸ ባህሪዎችን የሚያቀርቡት አስደናቂ የአደይ ተዋንያን በእምነት ሙሉጌታ እና ሰርካለም ጌታሁን በአቦል ቲቪ ኦፊሻል ፌስቡክ ፔጅ ላይ በላይቭ ቻት ያግኟቸው!

በእምነት ሙሉጌታ የምትተውነው የ17 አመት ልጃገረድ አደይ፣ በእንጀራ እናቷ አዲስ አበባ ውስጥ የታዋቂ ፋሽን ዲዛይነር ቤተሰብ የሞግዚትነት ስራ እንድትቀበል ትታለለች። ትዕይንቱ የሚከተለው አደይ በከተማ ውስጥ የሚጠብቃትን ችግር ለማለፍ እና ህልሟን ለማሳካት ስትጥር ነው።

ከበእምነት ጋር ማውራት ይፈልጋሉ? ሰኔ 11 አርብ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ ፌስቡክ ላይቭ ላይ በእምነትን ለማግኘት ይዘጋጁ።

በተጨማሪም ለውድ ተመልካቾቻችን በአደይ ላይ ወ/ሮ ሮማን ሆና የምትጫወተው ሰርካለም ጌታሁን ሰኔ 18 አርብ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ ፌስቡክ ላይቭ ትቀርባለች። ይሄ ጊዜ ስለተወዳጁ ድራማ አደይ እስካሁን ማወቅ የሚፈለጉትን ነገሮች ሁሉ መጠየቅ የምትችሉበት ሰዓት ነው።

ይሄን ፕሮግራም ለወዳጅ ዘመዶቻቹ እንድታሳውቁ እንጋብዛለን! አርብ ምሽቶች በጉጉት ይጠብቁ። በአቦል ቲቪ ኦፊሻል ፌስብክ ፔጅ ላይ ሰኔ 11 እና 18 አርብ ከምሽቱ 1:30 ያግኙን።