abol tv logo

የአቦል አዲሱ ሲትኮም አስኳላ

ዜና
04 ሜይ 2021
አስኳላ ኢትዮጲያውያንን እያሳቀና እያዝናና ይገኛል!

አስኳላ የሃገሪቱን ኮሜዲ ወዳጆች ለየት ባለ አቀራረብ ላለፉት ሁለት ሳምንታት እያዝናና እና እያሳቀ ይገኛል። ሲትኮሙ የሚከተለው መደበኛ ትምህርት ስላልተማሩ የእድሜ ልክ ፀፀት ያለባቸው የኔታ በላይ ስተባሉ የሃይማኖት አባት ነው። ከዚህ የፀፀት ስሜት ለመውጥት የኔታ በላይ በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ አንደኛ ክፍል ይመዘገባሉ።

ያለፉት ሁለት ክፍሎች በአስኳላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የኔታ ሲመዘገቡ እና በዚህ አዲስ አከባቢ ውስጥ ስለሚያጋጥማቸው የተለያዩ ገጠመኞች አይተንበታል። የትዕይንቱ ጅምር ስኬታማ ነበር፣ ልዩ ገጸ ባህሪያቱ እና አስቂኝ አቀራረብ በማህበራዊ ሚዲያ ተወዳጅ ነበር!

የአቦል ቲቪ ተመልካቾች ይሄን ብለዋል፡

በአስኳላ ምን እንዳዝናናችሁ አስተያየት ይስጡን።

አስኳላ እሮብ ከምሽቱ 1:30 አንዳያመልጥዎ!