Logo
Quchit S1

እረጅሙ ጨዋታ - ቁጭት

ዜና
13 ፌብሩወሪ 2024
መሰለ በተለያዩ ተጨዋጮች ከጨዋታው እንዲወጣ እየተገደደ ነው። ነገር ግን እሱ ሁሌም ሁለት እርምጃ እየቀደማቸው ይገኛል። እንዴት እንደዚህ ማድረግ እንደቻለ እንመልከት።
the long game - quchit article

መሰለ ብልህ እና ታጋሽ ባህሪ ያለው ገጸ ባህሪ ነው። እስካሁን በቁጭት ድራማ የተከሰቱት ነገሮች የእሱን ህይወት እያወሳሰቡት ሄደዋል። እረጅም ጨዋታ ማለት የተቀናቃኝን ቀጣይ እርምጃ ማወቅ ብቻ ሳይሆን የሚቀጥሉት ሁለት እርምጃዎችን አልፎ እርምጃ መውሰድ ነው። በቁጭት ድራማ እረጅሙን ጨዋታ በአስገራሚ መንገድ እየተጫወተው ያለው ገጸ ባህሪ መሰለ ነው። የመሰለን ሶስት አስገራሚ እርምጃዎችን እንመልከት፡

  1. ተሰማ እና እታፈራውን ግንኙነት ማወቁ

ሰለ በተደጋጋሚ እንዲረዳው የሚጠቀመው ኢንቨስትጌተር አለው። ይህ መረጃ ሁሌም እንዲኖረው እና ለምንም አይነት ችግር እንዲዘጋጅ አድርጎታል። በዚህ ጉዳይ ግን የተሰማ ህይወት እንደሚያስመስለው ንጹ እንዳልሆነ እና የእታፈራው እጅ እንዳለበት መድረስ ችሏል። ይህ መረጃ ደግሞ ዮናስ ስራውን እንዳይለቅ ለማድረግ ጠቅሞት ነበር።

  1. ዮናስን አሳስሮ ለምርጫው ተቃውሞ እንዲያቀርብ ማድረግ

የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ለመሆን ተሰማ እና እታፈራው ብዙ ጥረት እያደረጉ ነበር። በዚህ መሀል መሰለ ስለ ግንኙነታቸው እውነቱን ፈንቅሎ አውጥቶ፣ እታፈራውን መንበረ እንድትጠራጠራት አድርጓል። በተጨማሪም ዮናስ ሊሰማው ስላልፈለገ አሳስሮት ዮናስ በንዴት ለተሰማ ድጋፍ እንዲሰጥ አድርጓል። ዮናስ ድምጹን ለተሰማ እንዲሰጥ ደረገበት ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ ምርጫውን በእራሱ መንገድ ማሸነፍ ችሏል።

  1. አሰግድ የሮቤልን ሼር መግዛቱ

ከአሰግድ ጋር ባልተጠበቀ ሁኔታ አብሮ መስራት ሲጀምር ታዳሚውን ግራ አጋብቶ ነበር። ነገር ግን መሰለ አሁንም ከሁሉም ሰው በላይ ዝግጅት ያደረገበት ነገር ነበር። ለአሰግድ ኮትራክቱን በመስጠጥ ሼሩ በስሙ እንዲዞር አድርጓል። ይህ ስምምነት አሰግድንም፣ መሰለንም የሚጠቅም ነው።

መሰለ በአስገራሚ ሁኔታ የተለያዩ ገጸ ባህሪያትን አታሎ አሁን ወደአለበት ቦታ ደርሷል። ነገር ግን እነዚህ ገጸ ባህሪዎች መታለላቸውን ከደረሱበት ምን ያደርጉ ይሆን? በጥንቃቄ የገነባው የውሸት አለም ይፈርስ ይሆን?

የመሰለን ታሪክ በቁጭት ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉ!

#MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed