Logo

በየካቲት ወር እነዚህን አቅርቦቶች በአቦል ቲቪ ይጠብቁ

ዜና
09 ፌብሩወሪ 2024
የፍቅረኛሞች ወር አቦል ቲቪ ልብ ሰቃይ አቅርቦቶችን ይዞ መጥቷል።
what to watch feb 2024

የ2016 / አጋማሽ ላይ ደርሰናል እናም አቦል ቲቪ ድንቅ ድራማ፣ ኮሜዲ እና ሪያሊቲ ትርኢቶችን ማቅረቡን ቀጥሏል።

በመጀመሪያ የአቦል ቲቪ ታላቅ ፕሮዳክሽን አፋፍ ድራማ ላይ ታማኝነት እየተፈተነ እና አዲስ አጋርነት እየተመሰረተ ነው። ባልተጠበቀ መንገድ አዲስ ከእስከዳር ጋር መስራት ጀምሯል እናም ኢታናያን አግቶ አባቷን በማሰቃየት እስከዳርን እረድቷታል። በሌላ በኩል ደግሞ እንቆጳ ታምራትን መጠርጠር ጀምራለች እናም ፍቅሩን መቀበል አልፈለገችም። ታምራት ፍቅሩ ንጹህ እንደሆነ እንቆጳን ያሳምናት ይሆን ወይስ በመጀመሪያ ደረጃ አሰውነቱ ይጋለጣል? አፋፍ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉ!

ሁለተኛው ቁጭት የቤተሰብ ድራማ በፈጣን ታሪኩ የታዳሚዎችን ልብ ሰቅሎ ይገኛል። ዮናስ አቶ ፀጋዬ አባቱ መሆኑን ካወቀ በኋላ አብረው ጊዜያቸውን ሳያጣጥሙ አቶ ፀጋዬ በድንገት ሞተዋል። ነገር ግን ይህ ሀዘን ቤተሰቡን አንድ ያደርጋል ብሎ ሲታሰብ የአቶ ፀጋዬ ባለቤት ድርጅቱን የእራሷ እና የልጆቿ ለማድረግ ትጥራለች። ዮናስ መሰለን ከመንበረ ዛቻ እየተከላከለ ሲመስለው ስለ መሰለ ድብቅ ስራ ይደርስበታል። ዮናስ መሰለ የዋለለትን ውለታ በማሰብ አሁን የደረሰበትን ነገር ይረሳል ወይስ መሰለን ይበልጥ መጠርጠር ይጀምራል? ቁጭት ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው የሁለት ጠበቆች ታሪክ በዳግማዊ ይቀርባል። የዳግማዊ እና ዳንኤል በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸው ተለውጧል፣ የተበደሉ ሰዎችን በመከላከል እየረዱ እያለ አንድ ታመነ የተባለ ባለስልጣንን ሲከሱት ቢሮዋቸው መጥቶ በጥይት ይመታቸዋል። የዳንኤልን ህይወት ለማትረፍ ዶክተሮች ጥረት ቢያደርጉም ሊያተርፉት አልቻሉም። ዳግማዊ በከፍተኛ አደጋ ሆስፒታል ተኝቶ የጓደኛውን ሞት አልሰማም፣ እነዚህ ጠበቃዎች በመጨረሻ ፍትህ ያገኙ ይሆን? የዳግማዊን የመጨረሻው ክፍል ሰኞ ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!

እንቁጣጣሽ የሁለት ቤተሰብን ምስጢራዊ ታሪክ እንቁ እና ሰላም ሊደርሱበት ይሞክራሉ። ሰላም እና እንቁ የአያቶቻቸውን ጠብ ያስከተሉትን ምስጢሮች ለመግለጥ የቤተሰቦቻቸውን ጠላትነት ትተው ጓደኛሞች ይሆናሉ። ነገር ግን ቤተሰቦቻቸው ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች መልስ መስጠት አይፈልጉም። በዚህም ማሃል እንቁ ያስቀየመችው ገንዘብ ተበዳሪ ሊበቀላት በማታ ይመጣል። እንቁ የቤተሰቧን ምስጢር ትደርስበት ይሆን? እንቁጣጣሽ ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው አዲሱ የአቦል ቲቪ ድራማ የውሃ ሽታ ልብ እንጠልጣይ ታሪኩን ይቀጥላል:: የውሃ ሽታ የፀሎትን የሞት ታሪክ እና በማስታወሻዋ የተዘረዘሩትን የገዳዮቿን ማንነት የሚያቀርብ ድራማ ነው። ሮቤል የፀሎትን ማስታወሻ ማንበብ ጀምሯል እና እናቱ ያላገኘችውን ፍትህ በፀሎት ለማግኘት ቆርጧል። የመጀመሪያዋ ተጠርጣሪ ፍሬ ነበረች ፣ ሮቤል የፀሎትን ገዳይ ማግኘት ይችል ይሆን? የውሃ ሽታን ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!

በየካቲት ወር አቦል ቲቪ እነዚህን እና ሌሎች ድንቅ አቅርቦቶችን ይዞ ይቀርባል። እርስዎ በፍቅር ስለሚከታተሉትን ድራማ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻችን አስተያየትዎን ይላኩ! #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed