Logo
Quchit S1

ቁጭት ድራማ የመጀመሪያ ክፍል እይታ

ዜና
21 ኖቬምበር 2023
ቁጭት ድራማ በአቦልት ቲቪ ጀምሯል።
quchit first look article

ሰኞ ኅዳር 10 በአቦል ቲቭ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ቁጭት ኦሪጅናል የቤተሰብ ድራማ ጀምሯል። ድራማው የሚያጠነጥነው በሶስት ቤተሰቦች ታሪክ ላይ ነው። እነዚህን ቤተሰቦች እና ገጸ ባህሪያት እንተዋወቅ!

Quchit S1
quchit poll 2

ከእነዚህ ሶስት ገጸ ባህሪያት ማንን ነው የወደዱት?

quchit first look article
ዮናስ29%
mr tsegaye - quchit
አቶ ፀጋዬ57%
mr melese - quchit
አቶ መሰለ14%

ዮናስ 

ዮናስን ስንተዋወቅ ስለ ገጸ ባህሪው ሶስት ነገሮችን ተምረናል። በኢንጂነሪንግ ስራ ላይ የሚሰራ ብልህ ሰራተኛ ነው፣ ስለ የእንጀራ ወንድሙ ልጅ ሄዋን ደህንነት ይጨነቃል የእንጀራ አባት ቤተሰብ እያንገላታው ነው የሚኖረው። እነዚህ ነገሮችን በማወቅ የዮናስን ገጸ ባህሪ በፍጥነት እንድንወደው ተገደናል። በመጀመሪያው የቁጭት ክፍል ላይ እንዳየነው ግን ዮናስ ሄዋንን በመከላከሉ ከቤቱ ተባሯል። በተጨማሪም የእናቱ ፎቶ ከአቶ ፀጋዬ የድሮ ፍቅረኛ ጋር ይመሳሰላል። ስለዚህ ዮናስ የአቶ ፀጋዬ ልጅ መሆኑን አውቀናል። አባት እና ልጅ የሚተዋወቁ ይመስልዎታል?

አቶ ፀጋዬ

አቶ ፀጋዬ ድርጅታቸውን ከአባታቸው ወርሰው እያስተዳደሩት ኖረዋል። በመጀመሪያው የቁጭት ክፍል ላይ፣ ቢሮዋቸው ውስጥ ወድቀው ሆስፒታል ይሄዳሉ። በዚህ ጊዜ የካንሰር ታማሚ መሆናቸውን እናውቃለን። አቶ ፀጋዬ ይሄን ዜና ለቅርብ ጓደኛቸው አቶ መለሰ ብቻ ይነግሯቸዋል። ለቤተሰባቸው መናገር ያልፈለጉበት ምክንያት ምን ይሆን?

አቶ መሰለ

አቶ መሰለ ከአንድ ልጃቸው ዳግም ጋር የሚኖሩ እና ከአቶ ፀጋዬ ጋር የሚሰሩ መሆኑን አውቀናል። ነገር ግን ደስተኛ ምስል የሚያሳየው ቤተሰባቸው ችግር አለበት። አቶ መሰለ ልጃቸው ዳግም ላይ በትምህርት ጉዳይ የሚያደርጉት ጫና ዳግምን ወደ አላስፈላጊ ድርጊቶች እየገፋፋው ነው። በተጨማሪም አቶ መሰለ ስለ አቶ ፀጋዬ የድሮ ፍቅረኛ እና የዮናስ እናት መዐዛ መለያየት የሚያውቀው ነገር ያለ ይመስላል። አቶ መሰለ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሆን የሚያውቀው?

የመጀመሪያው የቁጭት ድራማ በጣም መሳጭ እና አዝናኝ ነበር። በተጨማሪም የክፍሉ መጨረሻ ልብ አንጠልጣይ ነበር፣ ክፍል ሁለትን በጉጉት እየተጠባበቁ ነው?

አስተያየትዎን በማህበራዊ ሚዲያ ገጻችን ኮሜንት በማድረግ ያሳውቁን!

 

ቁጭት ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!