Logo

አቦል ቲቪ ጋር ሁሌም አዲስ አቅርቦት እናጣጥም

ዜና
10 ኖቬምበር 2023
አንድ አይደለም ሁለት ግን አምስት አጓጊ አቅርቦቶች ወደ አቦል ቲቪ መጥተዋል።
new shows on abol - nov 2023

በዲኤስቲቪ ቻናል 465 ከመጀመሩ ከሁለት አመት በኋላ አቦል ቲቪ ለተመልካቾች ምርጥ ዝግጅት ማቅረቡን ይቀጥላል። በዚህ ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ይዘት ዘርፎች ያሉ ድራማዎችን አቅርቧል። በዚህ ሁለት ወር የሚቀርቡት ዝግጅቶችም የተለያየ ይዘት ያላቸው ሲሆኑ ተመልካቾችን እንደሚያዝናኑ ጥርጥር የለውም።

ቁጭት - ሰኞ ኅዳር 10 ከምሽቱ 2:30 ይጀምራል

ቁጭት የአቦል ቲቪ አዲስ እና የተለየ ቴሌኖቬላ በቅርብ ቀን ይጀምራል። በቁጭት ቴሌኖቬላ ስለ አባቱ ምንም እዉቀት የሌለው ዮናስ ከእንጀራ አባቱ ጋር በተፈጠረው ፀብ ምክኒያት ከገባበት ችግር ለመዉጣትና ህይወቱን ለማስተካከል ለረጅም ጊዜ እምቢ ወዳለው የቅጥር ስራ ፊቱን አዙሮ መስራት ይጀምራል። የ ዮናስ የእለት ተእለት ዉጣ ዉረዶችን እና አቶ ፀጋዬ የማያዉቁት ልጃቸውን ለማግኘት የሚያደርጉት ዉጣ ዉረድን እየቃኘን እንጓዛለን።

ዳግማዊ - ሰኞ ኅዳር 10 ከምሽቱ 3:00 ይጀምራል

ዳግማዊ በአንድ ወቅት በሀዋሳ ከተማ አጋጥሞ በነበረ እውነተኛ ታሪክ ላይ በተጻፈው ዳግማዊ መጽሐፍ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ሲሆን ስለ ተጨባጭ ፍትህ ሲባል አደጋን ስለተጋፈጠው ወጣት ጠበቃና ጓደኛው የሚተርክ ነው፡፡ የእነርሱ አሳዛኝ፣ ነገር ግን ደፋር ጉዟቸው በመማር ልምድ፣ በፈተናዎች እና አስደንጋጭ ድርጊቶች የተሞላ ሲሆን ይህ እውነተኛ ታሪክም ተመልካቾችን እንደሚያስደንቅ ጥርጥር የለውም።

ፅናት

በአሳዳጊዋ ተንገላታ እና በከፍተኛ ቁጥጥር ውስጥ የምትኖር አንዲት ወጣት እውነተኛ ቤተሰቧን ማፈላለግ ትጀምራለች። ይህ አጓጊ ታሪክ በአቦል ቲቪ ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3፡00 ይቀርባል።

ሻክሚ

ሻክሚ ሪያሊቲ ሾ ያልተዳሰሰውን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ልዩ ውበት ይዞ ይቀርባል። ከተለያዩ ብሄረሰቦች እና ባህሎች የሚመጡ አርቲስቶች እና ሙዚቃ ያቀርባል። ይህ አዝናኝ ዝግጅት ዘወትር ሀሙስ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ ይቀርባል።

ቀይዋ ቀን

ይህ አስቂኝ ድራማ 3ኛ ምዕራፍ ይዞ ቀርቧል። ቀይዋ ቀን በሶስት የፖሊስ መኮንኖች ስራ እና የግል ህይወት ላይ ያተኮረ አስቂኝ ድራማ ነው።

እርስዎ ከእነዚህ አዳዲስ አቅርቦቶች የትኛውን ወደውታል? በማህበራዊ ሚዲያ ገጻችን ኮሜንት በማድረግ ያሳውቁን! አቦል ቲቪ በዲኤስቲቪ ናል 465 ይመልከቱ