Logo
agarochu s2
channel logo

Agarochu

465RealityPG13

የአጋሮቹ 3 አስደናቂ ውድድሮቹ

ዜና
08 ዲሴምበር 2023
አጋሮቹ ውድድር ለየት ባለ መንገድ የጥንዶችን ፍቅር እና ችሎታ ይፈትናል።
agarochu 3 fun challenges article

አጋሮቹ የጥንዶች ውድድር ሁሉንም ዙር አልፈው ላሸነፉ ጥንዶች ድል ያለ ሰርግ የሚደግስ ዝግጅት ነው። በአጋሮቹ ላይ ልዩ ልዩ ጥንዶች ቀርበው የፍቅር ታሪካቸውን እና ለምን እንደሚወዳደሩ አጋርተውናል። እስካሁን ከቀረቡት ውድድሮች በጣም አስደናቂ ነበሩ ብለን ያሰብናቸው ውድድሮች እነዚህ ናቸው፡

  1. እግር ኳስ ጨዋታ

እግር ኳስ ጨዋታ ያን ያህል አስደናቂ ውድድር አይደለም ብለው ሊያምኑ ይችላሉ። ነገር ግን ይህ ጨዋታ አስደናቂ ያደረገው ሜዳው ጭቃ መሆኑ እና በዚህ ውስጥ ነፃ ሆነው እንዲጫወቱ እየተፈተኑ የነበሩት ጥንዶች ናቸው። ሳናስበው ተመስጠን አንዱን ቡድን እንድንደግፍ ያደረገን ፍልሚያ ነበር። ውድድሩን ይመልከቱት፡

  1. ሌሎች ተወዳዳሪዎች ጋር ዴት መውጣት

ይህ ያልተጠበቀ ውድድር የተዘጋጀው ጥንዶቹ እርስ በራስ ላይ ምን ያህል እምነት እንዳላቸው ለማወቅ ነው። ጥንዶቹ ውድድሩ ሲነገራቸው የመሳተፍ ፍላጎት የላቸውም ነበር ነገር ግን ለማሸነፍ ብለው ተሳትፈዋል። ውድድሩን ይመልከቱት

agarochu s2
agarochu s2 poll 7

እርስዎ ለውድድር ብለው ከሌላ ሰው ጋር ዴት ይወጣሉ?

አይ50%
አዎ 50%

  1. በሰርግ ልብስ ሩጫ

ጥንዶቹ በሩጫ ውድድር ላይ ይቀርባሉ ነገር ግን ሩጫው ላይ መሳተፍ ያለባቸው የሰርግ ቀሚስ እና ሱፍ አድርገው ነበር። ይህ ውድድር የጥንዶቹን አብሮ መስራት መቻል እና እርስበራሳቸው ያላቸውን ድጋፍ ይፈትን ነበር። አስደናቂውን ውድድር ይመልከቱ

እስካሁን በአጋሮቹ ልዩ ልዩ ውድድሮችን አይተናል እናም ይበልጥ አስደሳች ውድድሮችን እንጠብቃለን። እርስዎ የትኛውን ውድድር ነበር የወደዱት?

አጋሮቹ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!