Logo
Gizze S1
channel logo

Gizze

465TelenovelaPG13

ከጊዜ ድራማ የወደድናቸው 3 ነገሮች

ዜና
15 ኖቬምበር 2023
የጊዜ ድራማን ፍጻሜ በማስመልከት ስለድራማው የወደድናቸውን 3 ነገሮች አቅርበናል።
3 things we love about gizze article

ጊዜ ድራማ የሚያጠነጥነው ጀምበሩ በተባለ ባልፈጸመው ወንጀል ምክንያት ለ20 አመታት ታስሮ የተፈታ ገጸ ባህሪ ነው። ጀምበሩ በቅርብ ጓደኛው እና የስራ ባልደረባው ጌታቸው ባልፈጸመው ወንጀል እንዲታሰር ተደርጎ ነፃነቱን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡንም፣ ድርጅቱንም ተቀምቷል። ጀምበሩ እስካሁን የቤተሰቡን እና በአካባቢው ያሉ ሰዎችን እምነት እያገኘ ቆይቷል በተጨማሪም ከ20 አመታት በፊት ወንጀሉን አለመፈጸሙን ለማስመስከር ይጥራል። ጊዜ ድራማን በፍቅር እና በጉጉት እንድንመለከተው ያደረጉንን 3 ምክንያቶች ደግሞ እነዚህ ናቸው።

የጀምበሩ ገጸ ባህሪ

ጀምበሩ በሕይወቱ በሚቀኑበት ሰዎች ምክንያት 20 ዓመት ያለወንጀሉ የታሰረ ከእስር ከወጣ በኋለ ለቤተሰቡ እውነታውን ለማሳወቅ በሚያደርገው ጉዞ ከባድ ፈተተና ያለፈ ሲሆን ቤተሰቡን ጊዜውን እና ሁሉ ነገሩን የተነጠቀ ሰው ነው። ነገር ግን የጀምበሩ ገጸ ባህሪ እንደሚጠበቀው ተማሮ፣ እጅ ሰጥቶ እና ተስፋ ቆርጦ የሚኖር አይደለም። በተቃራኒው ሁሉን ቻይ፣ አስተዋይ፣ ይቅር ባይ እና ጥሩ ልብ ያለው ገጸ ባህሪ ነው። እኛም በዚህ ምክንያት የጀምበሩን ታሪክ ተመስጠን እንድንከታተል እና ከጀምበሩ ገጸ ባህሪ እንድንማር ሆነናል።

የገጸ ባህሪያት ቤተሰባዊነት

በጊዜ ድራማ የሚቀርቡት ገጸ ባህሪያት፣ የደም ዘመዶች ባይሆኑም እንደ ቤተሰብ የሆነው ቅርርባቸው የሚያስቀና ነው። በጀምበሩ መታሰር ህይወታቸው የተቀየረው የተለያዩ ገጸ ባህሪያት ጊዜ ድራማ ላይ ግን አንድነትን መርጠዋል። ተሻገር ጀምበሩን እንደ አባቱ አይቶ ለመርዳት ይሞክራል፣ ምዕራፍ ጀምበሩን እንዲረዳውም ለማድረግ ይሞክራል። ህሊና ለጀምበሩ ካላት ፍቅር ተነስታ ፍትህ እስከሚያገኝ ላለማረፍ ወስናለች። ሌሎችም ገጸ ባህሪያት ሁሌም ከጀምበሩ አጠገብ በመሆን ድጋፍ እንዲኖረው አድርገዋል።

የታሪኩ መሳጭነት

ለጊዜ ድራማ ተወዳጅነት ትልቁ ምክንያት የታሪኩ አጻጻፍ እና ማራኪ አቀራረብ ነው። ጊዜ ከመጀመሪያው ክፍል ጀምሮ የአንድ ገጸ ባህሪን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ገጸ ባህሪያት ላይ ያተኩራል። በተጨማሪም የእነዚህን ገጸ ባህሪያት ህይወት ከዋናው ታሪክ ጋር በማስተሳሰር ሁሉም ትዕይንት ምክንያት ያለው ነበር።

እነዚህ ምክንያቶች የጊዜ ድራማ ታሪክ ለምን ተወዳጅ እንደነበረ ያስመሰክራል። የመጨረሻው የጊዜ ድራማ ክፍል ዛሬ ማታ 2:30 በአቦል ቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!