Logo

ድብብቆሽ - አደይ

ዜና
19 ጁላይ 2021
የአምዴ ቤተሰብ ውስጥ የተደበቁ ሚስጥሮች።

ማኪና ፅጌሬዳ አደይ ከአቤል ጋር እንዳትገናኝ አብረው ብዙ ጥረት አድርገዋል።አሁን ግን ማኪ የቾምቤን ማንነት የአምዴ ቤተሰብ እንዳይደረስበት የምታደርገው ጥረት ፅጌሬዳን አጠራጥሯታል።

ፅጌሬዳ ከአቤል ጋር ያላት ግንኙነት እንዲቀጥል እና የምትፈልገውን ሁሉ በእጇ ለማስገባት ምንም ከማድረግ ወደኋላ አትመለስም። አቶ ግርማ ስምምነታቸውን ካፈረሱ ምን ታደርግ ይሆን?

የአምዴ ቤተሰብ ውስጥ ብዙ የተደበቁ ሚስጥሮች አሉ፣ አደይ ነፃነትን ሆና ከአምዴ ቤተሰብ ጋር ዳግም መቀላቀል ከቻለች የተደበቀውን ሚስጥር ትደርስበት ይሆን? ወይስ የሷ ሚስጥር ይጋለጣል?

ከአምዴ ቤተሰብ ውስጥ ንፅህናዋን የሚያምንበት ሰው እየደገፋት ነው፣ ግን አደይ ትክክለኛውን መረጃ እስከምታሰባስብ ነፃነትን ሆና መኖር ትችላለች? የፅጌሬዳ እና የአቤልን ግንኙነት ስታይ እራስዋን መቆጣጠር ካልቻለች እቅዷ ይበላሻል ።

አደይ እራስዋን ከነፃነት ነጥላ እንዴት እቅዷን እንደምታሳካ ለማየት ድራማውን ይከታተሉ!

አደይ ድራማ ከሰኞ እስከ አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይቀርባል።