Logo

አዲሱ ጉድ ፈላ ኮሜዲ ድራማ በአቦል ቲቪ

ዜና
26 ሜይ 2021
የጉድ ፈላ ገጸ ባህሪዎች እነማን ናቸው?

አዲሱ ጉድ ፈላ ኮሜድ በአቦል ቲቪ ዝነኛ እና ታዋቂ አርቲስቶችን ይዞላችሁ ቀርቧል። በዚህ ኮሜዲ ሸዋፈራው ደሳለኝ ፣ ዮሃንስ ተፈራ ፣ አለማየሁ በላይነህ ፣ ሜላት ነቢዩ እና ሌሎችም ተዋንያኖች ይሳተፉበታል! በዚህ የኮሜዲ ድራማ ውስጥ ልክ እንደ 65 አመት ሰው ባህሪ እና አለባበስ ያለው የ34 አመት ይትባረክ ልክ እንደ 18 አመት ልጅ የሚኖረው አባቱ ጋር የሚፈጠረውን አለመግባባት ይከተላል። ይትባረክ ከመስራቤቱ ልጅ ጋር በያዘው ፍቅር ሲሰቃይ ከአባቱ እና በድህነት ከሚኖሩ ግን ደስታ ሞልቶ የተረፋቸው ጎረቤት እናት እና ልጅ ምክር ይጠይቃል። የጉድ ፈላ ገጸ ባህሪያቶችን እንመለከታለን።

ወጣት ነኝ ባይ አባት

ሀይሉ በእድሜው ተወስኖ መኖር የሚይፈልግ አባት ሲሆን ልጁ ይትባረክ ግን እንደ ወጣት ለምን እንደማይኖር አይገባውም። 

ልጅ ይትባረክ

ይትባረክ በአባቱ አኗኗር ስለሚያፍር፣ አኗኗሩን ለማስተካከል ጥረት ያደርጋል ግን ሊሳካለት አልቻለም። ይትባረክ በእምነት የተባለች አዲስ የስራው ባልደረባ ጋር በፍቅር ሲወድቅ ግን ከአባቱ ምክር መፈለግ ይጀምራል።

ጎረቤቶቹ

ተስፋ እና እናቱ በድህነት እና ችግር ውስጥ የሚኖሩ ቢሆንም ደስታ የማይርቃቸው እና ጭንቀት የማያበዙ ሰዎች ናቸው።  

አዲሷ ልጅ

በእምነት ለስራዋ ትልቅ አክብሮት ያላት እና በስራ ሰዓት ቀልድ የማትወድ ሰው ነች። ጓደኛዋና የስራባልደረባዋ መቅዲ ግን ይዛ በምትመጣው አዘናጊ ወሬ ላለመመሰጥ ብዙ ጥረት ታደርጋለች።

ወሬ ወዳጇ ሰራተኛ

ወሬ ማውራት እና መስማት ያስደስታታል። የወሬ ፍቅሯን ሊያሟሉላት በማይችሉ ባልደረቦችዋ ስትማረር ጓደኛዋ በእምነት ስራ በመስራቤቱ ስተጀምር በዚህ ትደሰታለች።

 

ጉድ ፈላን በአቦል ቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ላይ አርብ ከምሽቱ 3:30 እንዳያመልጥዎ!